1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሁለተኛ ቀን የተራዘመው የናይጄሪያ ምርጫ

እሑድ፣ መጋቢት 20 2007

በናይጄሪያ ትናንት የጀመረዉ የፕሬዚዳንትና የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ምርጫ በአሸባሪዎች ጥቃት ጥላ ተጋርዶ ዋለ። በርካታ ናይጀርያዉያን ድምፅ ለመስጠት በምርጫ ጣብያ በራፍ ላይ ረጅም ሰልፍ ይዘዉ ታይተዋል።

https://p.dw.com/p/1Ez1E
Nigeria - nominierter Präsidentschaftskandidat Muhammadu Buhari und Goodluck Jonathan
ምስል U. Ekpei/AFP/Getty Images / AP Photo

የድምፅ መስጫ ካርዱን የሚያነበዉ መሣርያ ቴክኒካዊ እክል ስለገጠመዉ የድምፅ አሰጣጡ ሥነ-ስርዓት ለዛሬ እንዲዛወር ተደርጎ ዛሬም ምርጫ ሲካሄድ ነዉ የዋለዉ። በናይጀርያ ከተመዘገቡት 150, 000 የምርጫ ጣብያዎች ዛሬ በ 300 ጣብያዎች ነበር ምርጫ ለሁለተኛ ቀን የተካሄደዉ። በዚህ ምርጫ ወደ 70 ሚሊዮን የሚሆኑ ናይጀርያዉያን መመዝገባቸዉ ተገልጾአል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፉክክሩ አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን እና በተቀናቃኛቸዉ በቀድሞዉ ወታደራዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት በሞሃማዱ ቡሃሪ መካከል ነዉ።

የምርጫ ውጤቱ ተቀራራቢ እንደሚሆን ይጠበቃል። ምርጫው ለሳምንታት የዘገየው የናይጄሪያው አማፂ ቡድን ቦኮ ሀራም በቦርኖ፣ ዮቤ እና አዳማዋ ከተሞች አለመረጋጋት በመፍጠሩ ነው። ምርጫው በተጀመረበት ቅዳሜ ዕለትም በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። የጀርመን ዜና ወኪል የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በቦርኖ ከተማ ብቻ ቢያንስ 25 ሰዎች ተገድለዋል። ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን፤« ዲሞክራሲ ጠንካራ ተቃውሞ እና የሀሳብ ልዩነትን ይፈቅዳል። ነገር ግን ምርጫ በፍጹም ወደጦርነት መቂ,ር የለበትም ወይም ህዝቡን ዕርስ በዕርስ ለማጋጨት እና የምንወደውን ህዝብ ለመከፋፈል አይፈቀድም። »

Nigeria Präsidentschaftswahl 2015
ምስል picture-alliance/dpa/Tife Owolabi

ተፎካካሪያቸው ሙሐማዱ ቡሃሪ ፤ ፕሬዚዳንቱ እስካሁን በናይጄሪያ የሽብር ጥቃት እና ሙስናን ማጥፋት ባለመቻላቸው፤ ለውጥ አስፈላጊ መሆኑን በበኩላቸው እንዲህ ገልፀዋል።«የ16 ዓመቱ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር፤ የተስፋ መቁረጥ፣ የተስፋ ቢስነት እና የፍርሃት ጊዜ ነበር።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ