1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሁለት የተከፈለው ኦነግ ዳግም አንድ ሊሆን ነው።

ማክሰኞ፣ መስከረም 25 2003

ለሁለት የተከፈለው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አባላት እንደቀድሞ አንድ ለመሆን ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።

https://p.dw.com/p/PVks
ምስል AP

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር አባላት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ድርጅቱ ለሁለት ከተከፈለ ሁለት ዓመት ሆነው። ኦነግ ለሁለት ሲከፈል በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው በአንድ ወገን፤ በቀድሞ የኢትዮዽያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንን በነበሩት በብርጋዲዬር ጄነራል ከማል ገልቹ የሚመራው በሌላ ወገን ሆነው ሲካሰሱና ሲወነጃጀሉ ከርመዋል። ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተደረገው ስምምነት ሁለቱ ወገኖች እንደቀድሞ አንድ ለመሆን ተነጋግረዋል፤ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። በዚህም ዋናው ውህደት በአምስት ወራት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ተስማምተዋል። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳው ጌታነህ ፤ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ቃል አቀባይ የሆኑትን ዶክተር በያን አሶባንና፤ የብርጋዲዬር ጄነራል ከማል ገልቹ ኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ሌንጮ ባቲን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳው ጌታነህ

መሳይ መኮንን
አርያም ተክሌ