1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ለህዝብ ሲሉ የታሰሩ ሁሉ ይፈታሉ»: የአሮሚያ ፍትህ ቢሮ 

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ጥር 9 2010

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋርጦ እንደሚለቀቁ መወሰኑን ከትናንት በስቲያ አስታዉቀዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/2r2R7
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Deutsch

Fed+Reg Prisoners release - MP3-Stereo

በዚህ ሕደት የሚፈቱ ሁሉም ተጠርጣርዎች ሕገ-መንግሥቱን ወይም ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን  ለመናድ ሚና ያልነበራቸዉ፤ የሰዉ ሕይት ያላጠፉ ወይም ጉዳት ያላደረሱና ሌሎችም መስፈርቶች ማሟላት የቻሉ ብቻ መሆኑን አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል።

የአሮሚያ ክልል በበኩሉ በክልሉ ለሕዝብ ጉዳይ ሲሉ የታሰሩት ሁሉም ታሳርዎች እንደሚፈቱ የክልሉ የኮሙኒኬሼን ጉዳዩች ቢሮ ከትላንት ወድያ ምሽት በፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረዉ መረጃ ይፋ አድርጓል። የተፈረደባቸዉ እስረኞችም ይቅርታ እንደሚደረግላቸዉ፣ የተከሰሱት ክሳቸዉ እንዲነሳና በምርመራ ላይ የምገኙ ምርመራዉ እንድቋረጥ እንደሚደረግ የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ፤ የኦሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ሐላፍ አቶ ታዬ ዳንዳኣን ጠቅሶ ዘግቦታል። የሰዉ ህወት ያጠፉና ከባድ የአካል ላይ ጉዳት ያደረሱ ለደሕንነታቸዉ ሲባልና በተለየ መንገድ እርቅ እስከምደረግ እንደማይፈቱ ዘገባዉ ቢጠቁምም የፈዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ያስቀመጣቸዉን ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች አላካተተም።

የኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ብቻ 30ሽሕ ሰዎች መልቀቁን የሚናገሩት የፖለትካ ተንተኝና በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቬርስቲ የካዳምክ ጉዳዮች አማካሪ ዶክተር ሚልኬሳ ምዳጋ ይናገራሉ። በዝቡ የፖለትካ ጥያቄ ሲጠይቅ የኦኮኖሚ መልስ መስጠት ተገቢ አይደለም የሚሉት ዶክተር ምልኬሳ የዴሞክራሲና ሰባዓዊ መብት ጉዳዮች ሲነሱ «ብዙ ሰዎች ጥያቄዉን እንደ ራስ ምታት ይቆጥራሉ» ይላሉ።

ከኦሮሚያ ክልል በፈደራል እስርቤቶች የሚገኙት አብዛኛዉ የፖለትካ እስረኞች የተመሰረተባቸዉ ክሶች የ«ዉሸት ክስ» ነዉ የሚሉት የሕግ ባለሙያዉ አቶ በትሩ ድባባ ናቸዉ። በማስተር ፕላን ላይ ተቃዉሞ ያደረጉ ስለተቃወሙ ብቻ «ሰዉ ሳይግድሉ ሰዉ ገድለሃል» በሚል የሰዉ ህወት የማጥፋት ክስ እንደተመሰረተባቸዉ፣ በተመሳሳይም  ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ ሙከራ አድርገዋል በማለት «የዉሸት ክስ»  የተመሰረተባቸዉ እንዳሉም ባለሙያዉ ይጠቅሳሉ።

አቶ በትሩ ድባባ: «የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር የወሰደዉ ርምጃ የፌዴራል መንግሥት ያስቀመጠዉን ቅድመ ሁኔታዎቹን ከልሰዋል። ይህ ደግሞ ሊበረታታ የሚገባ ነዉ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግም ያወጠቸዉን መስፈርቶች ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ተመልሶ ቢከልሰዉ የሚል ሃሳብ አለኝ።»

በክልልና በፌዴራል የተሰጡት የሕግ ዉሳኔዎች ልዩነት ካላቸዉ በሁለቱ በኩል ያለዉ የሕግ መዋቅር ወጥ አለመሆኑን ያሳያል ሲሉ አቶ በትሩ ድባባ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ።

አቶ በትሩ ድባባ: «እዉነቱን ለመናገር፣ በዚህ ሐገር ዉስጥ ወንጀልን የሚቀጣ አንድ የወንጀል ሕግ ነዉ ያለነዉ። ግን የፈደራልና የክልል መንግስታት የእስረኞቹን ጉዳይ እየገለፁ ያሉበት ሁኔታ በፈደራልና በክልል  መንግስታት መካከል ልዩነት እንዳላቸዉ ያሳያል።

በመጀመሪያዉ ዙር ክሳቸዉ ተቋርጦ ይለቀቃሉ ከተባሉት 528 ተጠርጣሪዎች በፌዴራል ደረጃ 115 እንደምገኙ የተቀሩት ደግሞ ከደቡብ ክልል መሆናቸዉን የጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ መግለፃቸዉ ይታወሳል።ኦሮሚያን ጨምሮ ከሌሎቹ ክልልሎች ሥለሚፈቱት ሰዎች ብዛት እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ