1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማትና ተግዳሮቶቹ

እሑድ፣ ሰኔ 29 2006

የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን መሠረተ ልማት ዘርግቶ በአቅድ መንቀሳቀስ የሚፈለግና የተለመደም ጉዳይ ቢሆንም፣ የሚሠምረውም ሆነ ውጤታማ ሆኖ መገኘት የሚቻለው ፣ ሥራ በየረድፉ በሙያ በሰለጠ የሰው ጉልበት በተቀላጠፈ ሁኔታ ሲከናወን ነው።

https://p.dw.com/p/1CW4m
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ይህ በተለይ ከመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ሆኑ መሥሪያ ቤቶች በእጅጉ የሚጠበቅ ነው። ከሥርዓቶች ለውጥ ጋር የመንግሥት መ/ቤቶችን አያያዝም ሆነ አመራር የታዘቡ አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ የብቃት ማነስ ብቻ ሳይሆን ብልሹ አሠራርም ፣ ዕድገት ፈላጊዎች አጥብቀው የሚሹትን ውጤት ማስገኘት አልቻለም። የተባበሩት መንግሥታት የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ መታሰቢያ ዕለት ዘንድሮ ሰኔ 16 ቀን 2006 ነው ታስቦ የዋለው።የታዳጊው ዓለም ባልደረባ በሆነችው ኢትዮጵያ ደግሞ ፣ ዘንድሮ በተጨማሪ ለ 2 ሳምንታት እስከ ሰኔ 30 እንዲታሰብ በመደረጉ እስከዛሬም ሆነ ነገ ይዘልቃል ማለት ነው።

ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ የመንግሥት ተቋማትና ተግዳሮቶቹ፣ የዛሬው የውይይታችን ርእስ ነው ፣ ለዚህም እንግዶች ጋብዘናል፣ ከመንግሥት የሲቭል አገልግሎት ሰጪ ሚንስቴር በኩል ተሳታፊ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ፤ ሐሳባቸውን ግን በአጭሩ አካተናል ። ለዛሬው ውይይት ቀጠሮ አክብረው የተገኙልን 3 ተሳታፊዎች ፤ የተለያየ ሙያ ይኑራቸው እንጂ እንደማንኛውም ዜጋ የተጠቀሰው መ/ቤት ተገልጋዮች ናቸው። ወ/ሮ ራሔል አየለ ፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ኮንፈደሬሽን የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ፣ ዓለማየሁ አበበ፣ የባለራእይ ወጣቶች ማሕበር ሊቀመንበር ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ጋዜጠኛ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ናቸው።

ተክሌ የኋላ

አዜብ ታደሰ