1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሰላም ጥረት የሴቶች ተሳትፎ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001

በአውሮፓ ኮሚሽን አዘጋጅነት በዓለም ዙሪያ የሚከሰቱ የኢኮኖሚ ቀውሶችና የተፈጥሮ አደጋዎችን እንዲህም ግጭቶችን መከላከልና ለችግሮችም አፋጣኝ መልስ መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ብራሰል ቤልጅየም ውስጥ በቅርቡ ተካሂዷል ።

https://p.dw.com/p/I6PD
ምስል AP

ግጭቶችን በመከላከልና ቀውሶችን በማስወገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች እና ከፍተኛ ባለሞያዎች ፖሊሲ አውጭዎችና ምሁራን እንዲሁም የሲቪክና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች የሚካፈሉበት ይህን መሰሉ ስብሰባ በኮሚሽኑ አማካይነት ሲካሄድ የአሁኑ ሶሶተኛው ነው ። አንድ ሺህ ተጋባዥች በተገኙበት በዘንድሮው ስብሰባ ግጭቶችን በመፍታት እና ሰላም በማውረድ ጥረት ውስጥ የሴቶችና የሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጥተኛ ተሳትፎ ወሳኝነት ውይይት ተካሂዶበታል ። ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ

ገበያው ንጉሴ /ሂሩት መለሰ /ሸዋዬ ለገሠ