1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለንደን በጥቃት ማግሥት

ነጋሽ መሐመድ
ሐሙስ፣ መጋቢት 14 2009

እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ብሎ የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።ፖሊስ ከግለሰቡ ጋር አባሪ ተባባሪ ያላቸዉን ሰዎች ዛሬ ሲያስር መዋሉ ተዘግቧል

https://p.dw.com/p/2ZpvF
London Tag danach
ምስል Getty Images/C. Court

(Q&A) Londen Anschlag - MP3-Stereo

ለንደን ዉስጥ ትናንት በደረሰዉ ጥቃት ለሞቱ ሰዎች ቤተ-ሰቦችና ለተጎዱ ሰዎች የተለያዩ  መንግሥታት፤ ድርጅቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሐዘን መልዕክት እያስተላለፉ ነዉ።ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለዉ የተባለ አንድ ብሪታንያዊ በመኪና እና በጩቤ ባደረሰዉ ጥቃት ሰወስት ሰዎች ገድሎ፤ አርባ ያክል አቁስሏል።እራሱም በፖሊስ በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ብሎ የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።ፖሊስ ከግለሰቡ ጋር አባሪ ተባባሪ ያላቸዉን ሰዎች ዛሬ ሲያስር መዋሉ ተዘግቧል።ሥለ ጉዳዩ የለንደኑ ወኪላችንን በሥልክ አነጋግረነዋል።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ