1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአማራ ተፈናቃዮች የተላከ ርዳታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 2 2010

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በባህር ዳር ከተማ ለተጠለሉ የአማራ ተዋላጆች የ800 ሺህ ብር ርዳታ መደረጉ ተገለጸ። ተፈናቃዮቹ ከ500 በላይ ሲሆኑ አሁን ተሰባስበው በተጠቀሰው ስፍራ የሚገኙት ግን 160 አባወራዎች መሆናቸውን የተፈናቃዮቹ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2xVLE
Karte Äthiopien englisch

የ800 ሺህ ብር ርዳታ መደረጉ ተገልጧል

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በባህር ዳር ከተማ ለተጠለሉ የአማራ ተዋላጆች የ800 ሺህ ብር ርዳታ መደረጉ ተገለጸ። ርዳታውን ያደረገው በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎችን ለመቋቋም ከሀገር ውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያውን የተመሠረተው «ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውን መብት» የተባለው ድርጅት ነው። ተፈናቃዮቹ ከ500 በላይ ሲሆኑ አሁን ተሰባስበው በተጠቀሰው ስፍራ የሚገኙት ግን 160 አባወራዎች መሆናቸውን የተፈናቃዮቹ ኮሚቴ ሰብሳቢ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ከዋሽንግተን ዲሲ መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ