1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአፍሪቃዉ እና ለአዉሮጻዉ ህብረት የኤርትራዉያኑ ድርጅት የላከዉ ጥሪ

ዓርብ፣ ሰኔ 4 2002

ለኤርትራ ሰብአዊ መብት መከበር በሚል መቀመጫዉን በብሪታንያ ያደረገ አንድ የሲቢክ ድርጅት ለአፍሪቃ እና ለአዉሮጻዉ ህብረት የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ዉዝግብ እልባት እንዲያገኝ እንዲሁም

https://p.dw.com/p/NoFh
ምስል picture-alliance/ dpa

የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚፈጽመዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያቆም የበኩላቸዉን እንዲያደርጉ በደብዳቤ የጠየቀ መሆኑ ተመልክቶአል። የኤርትራዉያኑ የሲቢክ ድርጅት ለአዉሮጻዉ ህብረት ኮሚሽን ፕሪዝደንት ሁሴ ማኑኤል ባሮሶ እና ለአፍሪቃዉ ህብረት ሊቀመንበር ዦን ፒንግ ደብዳቤዉን የላከዉ በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ላይ አዲድ አበባ ላይ ያካሄዱትን የጋራ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ሁለቱም ለአካባቢያቸዉ ችግር ትኩረት እንዲሰጡ ለማሳሰብ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ታዉቋል። የደብዳቤዉ ይዘት ምን ይሆን? የብረስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ፣ አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ