1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለኢትዮጵያ ጫናዎች መፍትሄ የተጠራ ዉይይት

ሰኞ፣ ሰኔ 7 2013

በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመራሮቹ ትናንት ባደረጉት የበይነ መረብ ውይይት በኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘረውን ጫና ለመቋቋም የሃገሪቱን አቋም የሚደግፉ ወዳጆችን ማፍራት እንደሚገባ አመልክተዋል።በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማለፍ በተቀናጀ መልኩ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3uro2
USA Washington | Kapitol in Washington
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Cortez

«ኢትዮጵያን ፈተናዎች ለማለፍ መረባረብ ያስፈልጋል» አምባሳደር ፍፁም አረጋ


በመላ ዩናይትድስቴትስ የሚገኙ የማኅበረሰብና የተለያዩ አደረጃጀት መሪዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘሩ ያልተገቡ ያሏቸውን ጫናዎችን መቋቋም በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መከሩ።በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አመራሮቹ ትናንት  ባደረጉት የበይነ መረብ ውይይት በኢትዮጵያ ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ጫና ለመቋቋም የሃገሪቱን አቋም የሚደግፉ ወዳጆችን ማፍራት  የወጣቱን ድርሻም ማጠናከር እንደሚገባ አመልክተዋል።በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ  በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች ለማለፍ ፣በተቀናጀ መልኩ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።


ታሪኩ ኃይሉ 


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ