1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለከሰል ሲባል የዛፎች መጨፍጨፍ፤

ሰኞ፣ ግንቦት 6 2004

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰል ለማክሰል ሲባልና ለማገዶ ፍጆታ ሲባል በሚቆረጡ ዛፎች መበራከት የአገሪቱን የደን ሃብት ይዞት ከዕለት ወደዕለት እያመናመነዉ መሄዱ እየተነገረ ነዉ። ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማሞቂያ የህዝቡ የአኗኗር ስልት

https://p.dw.com/p/14vUc
ምስል picture-alliance/ dpa

ካልተለወጠ በቀርም ችግሩ በዚሁ ይዘት፤ ምናልባትም ከህዝብ ቁጥር መብዛት ጋ በተገናኘ ተባብሶም ሊቀጥል እንደሚችል ነዉ ጉዳዩን በቅርብ የሚያዉቁ ወገኖች የሚያመለክቱት። የማገዶ እንጨትና ከሰሉን ንግድት ለመግለፅም፤ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከድሬደዋ እንደዘገበልን፦ አንድ የተሽከርካሪዎች ሥምሪት ኀላፊ አንዱን ሾፌር ፤ «መልካ ለመድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስድብሃል ?» ብለው ቢጠይቁት፣ ባጭሩ፤ «እንደ አህያው ብዛት ነው» ብሎ ይመልስላቸዋል። ከገጠር ከተማ የተሽከርካሪዎችን አውራ ጎዳና በመዝጋት ከሰል ጭነው የሚጎርፉ አህዮችን ብዛት ለመግለጽ መሆኑ ነው። ለከሰል ሲባል ስለሚወድሙ አገር በቀል ዛፎች የቀረበው ዘገባ ዝርዝር ይቀጥላል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

አርያም ተክሌ