1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለገና የፕላስቲክ ወይንስ የተፈጥሮ ጽድ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2009

የአዉሮጳዉን የገና በዓል በመብራት እና ሌሎች ጌጣጌጦች ከተንቆጠቆጠዉ የገና ዛፍ ዉጭ ማሰብ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ደግሞ የገና በዓል ሲታሰብ በአብዛኛዉ በአሉ በሚከበርባቸዉ ሃገራት የገና ዛፍ ተፈላጊነቱ ጨምሯል።

https://p.dw.com/p/2Ut08
Kanada Weihnachtsbäume Natur vs Plastik
ምስል Jillian Kestler-D'Amours

Christmas tree Plastic tree or real? - MP3-Stereo

 ጥያቄዉ ግን የተፈጥሮዉ  ወይስ የፕላስቲኩ የሚለዉ ነዉ። ካናዳ ስትታሰብ ጥቅጥቅ ያለዉ አረንጓዴ ደኗ አብሮ ይታወሳል። በደን የታጠረች መሆኗ ግን የግድ ለገና የሚፈለገዉ ዛፍ ከዚያ ይመጣል ማለት አይደለም። በዚያም ላይ በየዓመቱ ዛፉን በመመድመድ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ ጫና ከመፍጠር ተደጋግሞ መጠቀም የሚቻለዉን የፕላስቲክ ዛፍ ለምን ለገና አንጠቀምም የሚሉ ወገኖችም ተነስተዋል። የዶቼ ቬለዋ ዩሊያን ኬስትለር ደ አሙርስ የፈረንጆቹ ገና በሚከበርበት ሰሞን ተዘዋዉራ ሰዎችን በዚህ ጉዳይ ላይ አነጋግራ ዘገባ አጠናቅራለች።

 ሸዋዬ ለገሠ /ዩሊያን ኬስትለር ደ አሙርስ

ነጋሽ መሐመድ