1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለግሪክ መላ ፈላጊዉ የአዉሮጳዉ ጉባኤ

ዓርብ፣ የካቲት 5 2002

የአዉሮጳዉ ኅብረት ቋሚ ፕሪዝደንት ሚስተር ኸርማን ቫን ሮምፖይ የጠሩት መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ ትናንት በብራስልስ ተካሂዷል።

https://p.dw.com/p/Lzzg
የአዉሮጳ መሪዎች በብራስልስምስል AP

በኅብረቱ የረጅም ግዜ የአኮኖሚ እቅድ እና በአሁኑ ወቅት በተለይ የዩሮ ተጠቃሚ የኅብረቱ አባል አገሮች ላይ በተጋረጠዉ የኢኮኖሚ ችግር በመወያየት የጋራ አቋም በመዉሰድ ተጠናቋል። ባለፈዉ ወር ስራቸዉን የጀመሩት ሮምፖይ የትናንትናዉን ስብሰባ በተለይ የጠሩት በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰዉን የፊናንስ ቀዉስ ለመቋቋም እና በተለይ በግሪክ በደረሰዉ ችግር ዙርያ ለመወያየት ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ/አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ