1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጠ/ሚኒስትር መለስ መግለጫ የRSF አስተያየት

ዓርብ፣ መጋቢት 10 2002

የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የአማርኛው ቋንቋ ስርጭትን ለማወክ ማቀዱን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ተቋም RSF ተቃወመ ።

https://p.dw.com/p/MXeB

የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ ዦን ፍራንሷ ዡልያርድ ዛሬ ለዶይቼቬለ ራድዮ በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የVOA ስርጭት እንዲታወክ ለማዘዝ እንደማያመነቱ ማስታወቃቸው አግባብ አይደለም ብለዋል ። ዕርምጃው የኢትዮጵያ ምርጫው በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ ለነፃ ጋዜጠኞች አስቸጋሪና አደገኛ ይሆናል ብለው እንደሚሰጉም ዡልያርድ ተናግረዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ