1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ  

ዓርብ፣ የካቲት 29 2011

አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3Egej
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋን ምርጫ ለዘንድሮ አስተላልፎ ነበር። ይሁን እና ዓመቱ ቢጋመስም በ2011 ይካሄዳል ስለተባለው የሁለቱ ከተሞች ምርጫ ከምርጫ ቦርድ በኩል የተሰማ ነገር የለም ይላል የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር። ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ ካነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አንዱ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል። ስለ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድን አስተያየት ለማግኘት DW ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያቀርብልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ተስፋለም ወልደየስ