1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ60ኛ ግዜ አለማቀፍ የፊልም ትርኢት በፈረንሳይ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 21 1999

ጥሩ በወይን እና ሻንፓኝ በመጥመቋ፣ ጥሩ ሽቶ በማምረቷ፣ በምትታወቀዋ ፈረንሳይ፣ የአለም ኮከብ የፊልም ተዋንያንን፣ ፊልም ቀራጮችን እና የፊልም አድናቂዎችን፣ ስታስተናግድ ከርማለች። ግንቦት 8 ተጀምሮ ግንቦት 20 የተጠናቀቀዉ የፈረንሳዩ የፊልም ድግስ ላይ የአለም ታዋቂ ከያንያን፣ ከተለያዩ አገር የመጡ ታዋቂ የፊልም ቀራጮች፣ ታዋቂ ሰዎች ተካፍለዉበታል

https://p.dw.com/p/E0mL
ሮማንያዊዉ አሸናፊ Cristian Mungiu
ሮማንያዊዉ አሸናፊ Cristian Mungiuምስል AP

ሰሞኑን፣ የፈረንሳይ ዋና ከተማ፣ በፓሪስ ምትክ፣ በደቡባዊ ያገሪቱ ክልል የምትገኘዉ፣ የካን ከተማ፣ መዲና ሆና የአገሪቷን እንግዶች ስታስተናግድ ከርማለች። በሜዲተራንያን የባህር ዳርቻ ላይ የምትገኘዋ፣ ካን ከተማ፣ በጋ የሚጅምርበትን ወራት አስታካ፣ ለ60ኛ ግዜ፣ የአለም አቀፉን፣ የፊልም ፊስቲቫል አካሂዳለች። በካን የአለም አቀፉ የፊልም ፊስቲቫል የጀመረ እለት በፈረንሳይ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን፣ የፊልም ድግሱ መጀመሩ ሲበሰር በደማቅ ስሜት ነበር። ዘንድሮ ለስድሳኛ ግዜ በፈረንሳይ ካን ከተማ የተካሄደዉ ይህ የፊልም ድግስ ከሁለተኛ አለም ጦርነት በፊት አንድ ግዜ እንደተካሄደ በታሪክ ተጽፎአል። ከሁለተኛ አለም ጦርነት ወዲህ ደግሞ፣ እ.አ ከ1946 አ.ም ጀምሮ የፊልም ትርኢቱ መታየቱ ቀጥሎአል።

በዘንድሮዉ የፊልም ድግስ ላይ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርጥ የተባሉ 22 የተለያዩ ፊልሞች ቀርበዋል። Golden Palm የተሰኘዉን የካን የፊልም ትርኢት የዉድድር ሽልማት ዘንድሮ ለመጀመያ ግዜ የሰላሳ ዘጠኝ አመቱ ሮማንያዊ የፊልም ቀራጭ እና አቀናባሪ Cristian Mungiu አሸናፊ ሆንዋል። ሮማንያዊዉ Cristian Mungiu አሸናፊ የሆነበትን ፊልም ርዕስ «4 ወር 3 ሳምንት እና 2 ቀን» የሚል ሲሆን አንዲት የሮማንያ ሴት ለህገወጥ ወርጃ ኮሚኒስቷ ሮማንያ ፈቃድን ስታገኝ ያሳያል።


በካኑ የፊልም ትርኢት ላይ ጀርመን ከአለፉት ግዚያት ሲነጻጸር ዘንድሮ በርከት ያለ ፊልም ያቀረበች ትመስላለች። በሃምቡርግ ከተማ ነዋሪ የሆነዉ፣ ትዉልዱን በቱርክ ያደረገዉ፣ ታዋቂዉ ጀርመናዊ የፊልም ቀራጭ እና አቀናባሪ Fatih Akin የደረሰዉን “Auf der andre Seite” በተሰኘዉን የጀርመንኛ ቋንቋ ፊልም በካን የፊልም ትርኢት እጩ፣ ሆኖ ቀርቦ በደረሰዉ ጥሩ የፊልም ጽሁፍ ሽልማት አግኝቶአል። እ.አ 1979 አ.ም በዚሁ የካን የፊልም ድግስ ላይ፣ Blechtrommles በተሰኘዉ የጀርመን ፊልም፣ Golden Palm ሽልማት ያገኘዉ ጀርመናዊ የፊልም ቀራጭና አቀናባሪ፣ ዘንድሮ ULZAHN የተባለዉን ፊልሙን ይዞ ለዉድድር ቀርቦ ነበር።

በደቡባዊ ፈረንሳይ፣ የሜዲተራንያንን ባህር፣ ተንተርሳ ወደ የምትገኘዉ፣ ካን ከተማ የፊልም ድግስ፣፣ የመጀመርያ ታሪክ፣ ስንመለስ፣ የዛሪ ስድሳ አመት፣ እ.አ 1939 አ.ም መስከረም 1 ቀን፣ በካን የፊልም ትርኢቱ የታየዉ። በዝያኑ እለት የጀርመን ጦር፣ ፖላንድን ለመዉረር፣ እንቅስቃሴዉን ጀምሮ፣ ሁለተኛዉ አለም ጦርነት የተቀሰቀሰበት ወቅት ነበር። በካን የጀመረዉ ይህ የፊልም ድግስ ተቋረጠ። ከሰባት አመት በኳላ፣ እ.አ በ1946 አ.ም ጦርነቱ ካበቃ በኳላ፣ በበልግ ወራት ላይ፣ ካን እንደገና የፊልም ድግሷን በመቀጠል የዛሪ ስድሳ አመት ለመጀመርያ ግዜ በፈረንሳይ ራድዮ ይህ ነበር የተሰማዉ.

« የካን የባህር ዳርቻ የፊልም ትርኢት፣ የጥበብ፣ የፋሽን፣ ከአለም ዙርያ የመጡ ምርጥ ከያኒያን የሚታዩባት እና ትልቅ ሽልማት የሚሰጥበት ድግስ ነዉ። በዛሪዉ እለት ከ19 አገራት የመጡ የፊልም ቀራጮች እና አቀናባሪዎች በዚህ የፊልም ትርኢት ላይ ለመሳተፍ ተገኝተዋል። ለዉድድር ከቀረቡት 120 ፊልሞች መካከል 70 ረጃጅም ፊልሞች እና 50 አጫጭር ፊልሞች ይገኙበታል»

በዚያን ዘመን፣ የዛሪ ስድሳ አመት ማለት ነዉ፣ ጀርመን እና ጃፓን፣ በካን የፊልም ትርኢት፣ የዉድድሩ ተጋባዥ አልነበሩም። የፊልም ዉድድሩም፣ ከተለያየ አገር ከተሰባሰቡ፣ ፊልሞች ሳይሆን ከአንድ አገር ከመጣ፣ ከተለያየ ፊልም ጋር በማወዳደር ነበር፣ አሸናፊዉ የሚመረጠዉ፣ በዝያን ወቅት፣ የዚሁ የፊልም ትርኢት ዉድድር ላይ፣ ዳኛ ሆነዉ ተቀማጭ ከነበሩት መካከል፣ Maurice Bessy በግልጽ እንዳስቀመጡት

«ዉድድሩ የነበረዉ ከአንድ አገር ከመጡ የተለያዩ ፊልሞች ብቻ ነበር። ለምሳሌ ስድስት ከፈረንሳይ የቀረቡ ምርጥ ከተባሉ ፊልሞች መካከል ነበር ዉድድሩ የሚካሄደዉ፣ ወይም ደግሞ ስድስትም ሆነ ሰባት የአሜሪካ ፊልሞች ለዉድድር ቀርበዉ ከሆነ እርስ በራሳቸዉ ይወዳደራሉ። ከሶቭይ ህብረት የመጡትም ሆነ ከእንግሊዝ የመጡትም ፊልሞች በዚሁ መሰረት ይወዳደራሉ። በመጨረሻ ከየአገሩ አሸናፊ የሆነ ይመረጥና እያንዳንዱ አገር የኦስካሩን ሽልማት ያገኝ ነበር»

የጀርመን ፊልም ቀራጮች እና አቀናባሪዎች፣ በካኑ የፊልም ድግስ እንብዛምም፣ ተሰላፊ አልነበሩም። በሰባዎቹ አመት መጨረሻ፣ የጀርመኑ የፊልም ቀራጭ Völker Schöndorff በካኑ የፊልም ትርኢት አሸናፊ በመሆን ሽልማቱን ወስዶአል። በመጨረሻ እ.አ 1984 አ.ም ጀርመናዊዉ Wilm Wenders , Paris Texas በተሰኘዉ ፊልሙ የካኑ የፊልም ድግስ ተሸላሚ ሆንዋል። በዚህ አመት ጀርመናዊዉ Fatih Akin በፊልም ትርኢቱ ለአሸናፊነት እጩ በመሆን ቀርቦ ነበር።

የ 69 አመቷ አሜሪካዊትዋ የፊልም አክተር Jane Fonda በፈረንሳይ ካን ከተማ በተካሄደዉ አለም አቀፍ የፊልም ፊስቲቫል ላይ ለሞያዋ ላበረከተችዉ ትልቅ አስተዋጽዎ ልዩዉን የካን ሽልማት ከፊስቲቫሉ ፕሪዝደንት Gilles Jacob ተቀብላለች። የካኑ ፊስቲቫል የዉድድር ሽልማት በተሰጠበት እለት ምሽት ጀርመናዊትዋ የፊልም ተዋናይ Diane Kruger የመድረክ መሪ በመሆን "Bonsoir, Good Evening, Guten Abend" በፈረንሳይኛ በጀርመነኛ እና በእንጊልዘኛ እንደምን አመሻችሁ በማለት ነበር የሽልማቱን ስነ ስርአት የከፈተችዉ።