1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ችግር

ሐሙስ፣ የካቲት 17 2003

ትሪፖሊ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እንደገለፁት ግን ቤንጋዚ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መገደል፥ መደብደብ መታሠራቸዉንም ሰምተዋል።እዚያዉ ትሪፖሊ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ኢትዮጵያዉያን መገደላቸዉንም ገልፀዋል

https://p.dw.com/p/R40C
የአዉሮጳ ዜጎች ከሊቢያ ሲወጡምስል picture alliance / dpa

ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለተለያየ ችግር መጋለጣቸዉን አስታወቁ።በተለይ ከቤንጋዚ ለዶቸ ቬለ የኤስ፥ ኤም ኤስ መልዕክት ያስተላለፉ ኢትዮጵያዉያን እንደሚሉት የከተማይቱ ነዋሪ ስደተኛ ኢትዮጵያዉያንን ቅጥረኛ ወታደሮች ወይም የቅጥረኛ ወገኖች እያሉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ደብድበዋል።ገድለዋልም።የቤንጋዚ የስልክ መስመር ባለመስራቱ መልዕክቱን ያስተላለፉትን ማነጋገር አልቻልንም።ትሪፖሊ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች እንደገለፁት ግን ቤንጋዚ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መገደል፥ መደብደብ መታሠራቸዉንም ሰምተዋል።እዚያዉ ትሪፖሊ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ኢትዮጵያዉያን መገደላቸዉንም ገልፀዋል።ነጋሽ መሐመድ ሁለት ስደተኞችን በስልክ አነጋግሯል።ሒሩት መለሰ ደግሞ ሌላ ሰወስተኛ ስደተኛ አነጋግራላች።
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ