ልብ፤ የሰዉነት ማሽን
ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2001ማስታወቂያ
ይህች ደም ዑደቱን ሳያቋርጥ እንዲዟዟር የምታደርገዉ የተፈጥሮ ማሽን እክል ሊደርስባት የሚችለዉ በአገልግሎት ብዛት ብቻ ሳይሆን ገና ከመወለድም የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ የልብ ህክምና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር በቀለ አለማየሁ ይናገራሉ። የተለያዩ ሰዎች ህይወት ሳይታሰብ በአጋጣሚ ሲያልፍ ቶሎ የሚጠየቀዉ የልብ ችግር ነበረበት ወይም ነበረባት? የሚለዉ ሲሆን ሲከሰት ድንገትነቱ ህይወትን ሊያሳልፍ የሚችልበት ሁኔታም በተደጋጋሚ ታይቷል። ይህን ከግምት አስገብተን ነዉ ልብን ስለሚገጥመዉ ጠንቅ ባለሙያዉ እንዲያብራሩልን ያደረግነዉ፤
ሸዋዬ ለገሠ/ ነጋሽ መሐመድ