1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 44ኛ ዓመት እያከበረ ነው

ሰኞ፣ የካቲት 11 2011

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 44ኛ ዓመት አክብሮ ውሏል። ዛሬ ጠዋት በመቐለ ሰማእታት ሐወልት ቅጥር ግቢ ሲዘከር የትግራይ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የህወሓት አመራሮች፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጣ ተሳታፊ ተገኝቶበታል፡፡

https://p.dw.com/p/3DbEm
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የሕወሓት 44ኛ አመት

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የትጥቅ ትግል የጀመረበትን 44ኛ ዓመት አክብሮ ውሏል። ዛሬ ጠዋት በመቐለ ሰማእታት ሐወልት ቅጥር ግቢ ሲዘከር የትግራይ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የህወሓት አመራሮች፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጣ ተሳታፊ ተገኝቶበታል፡፡ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት የትግሉ ሰማእታት ለመዘከር በመላው ትግራይ በተመሳሳይ ሰዓት የሕሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በሥነ-ስርዓቱ ላይ መልእክታቸው አስተላልፈዋል፡፡

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ


እሸቴ በቀለ 
ሸዋዬ ለገሠ