1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠራቀመ ብሶት

ረቡዕ፣ ግንቦት 22 2010

የአፋር ሕዝብ-ባጠቃላይ፤ ፊደል የቆጠረዉ ወጣት-በተለይ በመሪዎቹ መማራር ከጀመረ ዓመታት አስቆጥሯል።በደል፤ብሶት፤ጥያቄዉን በይፋ መግለፅ ከጀመረ ደግሞ ስድስት ወር።ማቀጣጠያዋ-የሠመራ ዩኒቨርስቲ የሰዉ ሐብት ልማት ኃላፊ ድንገት መሠወር ነዉ።አቶ ረሺድ ሳሌሕ።

https://p.dw.com/p/2ycr5
Äthiopien Afar - Smartphone Nutzung
ምስል DW/T. Waldyes

Afar-Protest - MP3-Stereo

የአፋር መስተዳድር ባለሥልጣናት በሕዝብ ላይ ያደርሱታል የተባለዉን የአስዳደር በደል፤እስራት እና እንግልትን በመቃወም የሚደረገዉ የአደባባይ ሰልፍ እና አቤቱታ እንደቀጠለ ነዉ።ትናንት በክልሉ ርዕሠ-ከተማ ሠመራ ዉስጥ ሠልፍ የወጡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤የከተማዋ እና የአጎራባች ከተሞች ነዋሪዎች አለአግባብ የታሰሩ እና ታፍነዉ የተወሰዱ ያሏቸዉ ሰዎች እንዲፈቱ፤ አምባገነን ያሉት የክልሉ አስተዳደር እንዲለወጥ ጠይቀዋል።የሰልፉን ሒደት የተከታተሉ እንደሚሉት ሠልፈኛዉን ለመበተን ፀጥታ አስከባሪዎች ተኩስ ከፍተዉም ነበር። በሰዉ እና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ግን የለም።ነጋሽ መሐመድ ዘገባ አለዉ።
የትናንቱን ሠልፍ፤ ከሰልፍ ያደረሰዉን ምክንያት በቅርብ የሚያዉቁ እንደሚሉት የአፋር ሕዝብ-ባጠቃላይ፤ ፊደል የቆጠረዉ ወጣት-በተለይ በመሪዎቹ መማራር ከጀመረ ዓመታት አስቆጥሯል።በደል፤ብሶት፤ጥያቄዉን በይፋ መግለፅ ከጀመረ ደግሞ ስድስት ወር።ማቀጣጠያዋ-የሠመራ ዩኒቨርስቲ የሰዉ ሐብት ልማት ኃላፊ ድንገት መሠወር ነዉ።አቶ ረሺድ ሳሌሕ።
                                     
አቶ ረሺድ በሰላዮች «ታፍነዉ ተወሰዱ» የምትለዋ መረጃ መሠራጨት ለዓመታት ተዳፍኖ የቆየዉን ብሶት እያግተለተለ ያሰጣዉ ገባ።----ሐጂ ስዩም ለረጅም ጊዜ የአፋር ክልል የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ፤ ባለፉት ሰዎት ዓመታት ደግሞ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር ናቸዉ።
                                  
ዉጪ የሚገኘዉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር የአፋር ሕዝብ ፓርቲ መሪ ዶክተር ሙሳ ኮንቴ እንደሚሉት 27 ዓመት የተጠራቀመዉ ብሶት እየገነፈለ ነዉ።---ሐጂ ስዩም እና አስተዳደራቸዉን በመቃወም በራሪ ወረቀቶች ሲበተኑ፤ ማመልከቻዎች ሲቀርቡም ነበር። -----------ከአስተዳደሩ የተገኘዉ መልስ ግን፤ የደረሰባቸዉ እንዳሉት፤ ጠያቂዎችን ማሰር ነዉ።
                                 
እስራቱ ግን ተቃዉሞዉን አጠናከረዉ እንጂ አላቀዘቀዘዉም።ትናንት ሰመራ ዉስጥ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፤ የከማዉ እና የአጎራባች ከተሞች ሕዝብ ባደባባይ ተሰለፈ።
                                        
ፀጥታ አስከባሪዎች ሰልፈኛዉን ለመበተን ተኩስ ከፍተዉ ነበር።ሰዉ እና ንብረት ግን አልተጎዳም።
                                      
ቀጥሎስ? ያነጋገርናቸዉ እንደሚሉት «ሕጋዊ» ያሉት ጥያቄቸዉ ተገቢዉን መልስ እስኪያገኝ ድረስ ተቃዉሟቸዉ ይቀጥላል።ዶክተር ኮንቴም  መፍትሔዉ አምባገነናዊ ሥርዓትን ማስወገድ ነዉ ይላሉ።ሐጂ ስዩም እና ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ሌሎች የአፋር መስተዳድር ባለሥልጣናትን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ደዉለን ነበር።ገሚሱ ሥልካቸዉ ዝግ ነዉ።ሌሎቹ አይመልሱም።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ