1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መሃይምነት ድራማ ክፍል 3 -የኤሊያስ ደብዳቤ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2005

ይህ ሴት ልጅ መማር አለባት በሚል ርእስ የጀመርነውና በትምህርትና በመሃይምነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ክፍል 3 ጭውውት ነው፡፡

https://p.dw.com/p/17w6P

ወጣቷ ልእልት ትምህርት አቁማ ቤት መዋል ከጀመረች ወደ ሁለት ሳምንት ገደማ አስቆጥራለች፡፡ የትምህርት ክፍያ ባለመፈፀሟ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ተስተጓጉላ እናቷን ፓስቲ በመሸጥና ሌሎች የጓዳ ስራዎችን በመስራት እናቷን እየረዳች ትገኛለች፡፡ ዛሬ አባቷ የሚጠብቁትን የልጃቸው ኤልያስ ደብዳቤ ደርሶ ከሆነ ፖስታ ቤት ሄዳ እንድትጠይቅ ልከዋታል፡፡ ደብዳቤው ደርሷል፤ ሁሉንም ነገር ደግሞ እዛው ይገኛል፡፡ ደብዳቤው ለአባቷ ከማድረሷ በፊት እዛው ቀዳ ለማየት ብትጓጓም ቀድማ ወደ ጓደኛዋ ዙሪያሽ መስሪያ ቤት አምርታለች። ጭውውቱን ያድምጡ።