1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መሃይምነት ድራማ ክፍል 4 -ትምህርትን ማጠናቀቅ

ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2005

የበማዳመጥ መማር ዝግጅት ተከታታዮች ሴት ልጅ መማር አለባት በሚል ርእስ የጀመርነው ተከታታይ ጭውውት ክፍል 4 ነው ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው፡፡

https://p.dw.com/p/17w6e

በተፈጥሮዋ ነፃ የሆነችውና በአገር አስጎብኚ ድርጅት የምትሰራዋ ዙሪያሽ በጓደኛዋ ልእልት የትምህርት ጉዳይ በእጅ አዙር አማካሪዋ መሆኗን የልእልት ቤተሰቦች ጠርጥረዋል፡፡ በመሆኑም የልእልት እናት ወ/ሮ መብራት ዙሪያሽን እየጠሏት በመሄዳቸው ልክልኳን የሚነግሩበት አጋጣሚ እየጠበቁ ነው፡፡ ዛሬ ጧት ዙሪያሽ ሁለት አውሮፓውያን አገር ጎብኚዎች ማለትም የ67 አመቱ ጡረተኛ አዛውንት አቶ Handrik እና የ62 አመቷ ባለቤታቸው ወ/ሮ Susanna ወደ ልእልት አባት የብረታ ብረት ድርጅት ይዛ ትመጣለች ብሎ የጠበቀ የለም፡፡ ምን ያጋጥም ይሁን? ክፍል 4 ጭውውቱን ተከታተሉ፡፡