1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መሃይምነት ድራማ ክፍል 5 -ስኬት አልያም ዉድቀት

ረቡዕ፣ መጋቢት 4 2005

የበማዳመጥ መማር ዝግጅት ታዳሚዎች ይህ በትምህርትና በመሃይምነት ዙሪያ የሚያጠነጥነውን ጭውውት ክፍል 5 ዝግጅታችን ነው፡፡

https://p.dw.com/p/17w71

የ15 አመቷ ልእልት ወደ ትምህርት ገበታዋ ተመልሳለች፡፡ ሆኖም ግን የአቶ ወልዳይ ቤተሰብ የተደሰተ አይመስልም፡፡ ልእልትን ትኩረታቸውን ነፍገዋታል፡፡ እናቷ ከብድርና ቁጠባ ተቋም የወሰዱትን ብድር መክፈል ካቆሙ ሶስት ወራትን አስቆጥሯል፡፡ በመሆኑም እናቷ ልእልት ትምህርቷን አቋርጣ ስላላገዘችኝ ነው ለዚህ የተዳረግኩት በሚል ስሜት በሷ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰዋል፡፡ አቶ ወልዳይም እንዲሁ እቤት ውስጥ ለልእልት ይሰጧት የነበረው ጊዜ እየቀነሱ መጥተዋል፡፡ የልእልት የክፍል ሀላፊዋ ዛሬ ሊያነጋግሯት ይፈልጋሉ፡፡