መሃይምነት ድራማ ክፍል 7 -ልጅ መማር አለባት
ሰኞ፣ መጋቢት 9 2005ማስታወቂያ
ልእልት ትምህርቷን ለመማር ወደ ታላቁ ከተማ ከገባች ጊዜ ጀምሮ የከተማውን ኑሮ ግራ እያጋባት ነው፡፡ በቂ የመኖሪያ ክፍል መከራየት ስለማይችሉ ከወንድሟ ጋ በአንድ ቤት ውስጥ መተኛቱ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመኪና ጋጋታና ጩህቱ፣ የተበከለ አየር ብቻ ከገጠር ወደ ከተማ ኑሮ ሽግግሩ ትንሽ ከብዷታል፡፡ ልእልት የጤና ትምህርቷን የትምህር ክፍል መቅረት እንደሌለባትና የወንድሟን ኑሮ ሳታናጋ በቁጠባ መኖር እንዳለባትም አምናለች፡፡
ሆኖም ግን አመታት ባለፉ ቁጥር የ18 ዓመቷ ልእልት ተፈጥሮአዊ ውበቷ ትኩረት መሳብ ጀምሯል፡፡ አሁን የመጨረሻው አመት ትምህርቷን በመከታተል ላይ ያለችው ልእልት ዛሬ ከወንድሟ ጋ ሃይለኛ ፀብ ውስጥ ገብቷል፡፡ አብራችሁን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡