1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስጊዶች በሮቻቸዉን ከፍተዉ ዋሉ

ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2000

የአለም ሙስሊሞች ታላቁን ቅዱስ የረመዳን ጾም በሚጾሙበት በአሁኑ ወቅት ሃሳብን አንድ በማድረግ ወደ ፊት በጋራ ለመራመድ መስጊድ አጣማሪ ድልድይ ነዉ በሚል መርህ ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ በጀርመን ዉስጥ የሚገኙ 2500 ያህል መስጊዶች እና የስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የሚጠቀሙባቸዉ ጸሎት ቤቶች ለጎብኝዎቻቸዉ በሮቻቸዉን ከፍተዉ ዉለዋል

https://p.dw.com/p/E0m5
በበርሊን የሚገኘዉ መስጊድ
በበርሊን የሚገኘዉ መስጊድምስል picture-alliance/dpa

በጀርመን ባለዉ የእስልምና ምክር ቤት የዝርዝር ማወቅያ ሰንጠረዥ መሰረት 3.3 ሚሊዮን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በጀርመን ይኖራሉ። 164 ያህል መስጊዶች እና 2500 ያህል አዳራሽ መሰል የጸሎት ማድረግያ ቦታዎች ይገኛሉ። በኖርድ ራይ ዊስት ፋልያ ግዛት በቁጥር በርከት ያለ ማለት 25 ያህል መስጊድ እንዳለ እና በርካታ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚኖሩበት የጀርመን ግዛት እንደሆነም ተገልጾአል። በጀርመን ጥንታዊ የተባለዉ መስጊድ በ Baden-Wüttemberg ግዛት Schwetzingen እንደ አ.አ 1783 የተገነባ ሲሆን 225 አመቱን የያዘዉ መስጊድም ነዉ ምንም እንኳ የመስጊድ ግንባታ በጀርመን ጥንታዊነት ቢኖረዉም በአሁኑ ወቅት በጀርመን በሚገኙ ታላልቅ ከተሞች መስጊድን ለመገንባት የተነሳዉ ሃሳብ አከራኪ ሲሆን ይታያል።
በጀርመን የሚገኙ መስጊዶች ለጎብኝዎች በሮቻቸዉን ከፍተዉ መዋላቸዉ ዛሪ የባህል መድረካችን በዋናነት የሚዳስሰዉ ርእስ ሲሆን በተጨማሪ በዶቸ ቬለ ራድዮ ጣብያ ሰራተኞች የሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በጀርመን ስላለዉ መንፈሳዊ ህይወታቸዉ ያጫዉቱናል መልካም ቆይታ