1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«መንግሥት የገባልንን ቃል አልጠበቀም »የቀድሞ የዴምህት ታጋዮች

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2012

በኢትዮጵያ ከተደረገው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ከኤርትራ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የቀድሞ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት) ታጋዮች በመንግስት ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለፁ፡፡ ታጋዮቹ ፓርቲያቸው በከፍተኛ አመራሩ 'በሕገወጥ መንገድ ከስሞ' ወደ ህወሓት መቀላቀሉንም ተቃውመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3caYn
Äthiopien Tigray Zalambessa | ehemaliger Mitglieder des Tigray People's Democratic Movement (TPDM)
ምስል DW/M. Haileselassie

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የቀድሞ ታጋዮች አቤቱታ

በኢትዮጵያ ከተደረገው የፖለቲካ ለውጥ በኋላ ከኤርትራ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት የቀድሞ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (በትግርኛ ምህፃሩ ዴምህት) ታጋዮች በመንግስት ቃል የተገባላቸው ድጋፍ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለፁ፡፡ ታጋዮቹ ፓርቲያቸው በከፍተኛ አመራሩ 'በሕገወጥ መንገድ ከስሞ' ወደ ህወሓት መቀላቀሉንም ተቃውመዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትን በሐይል ለመጣል ለዓመታት በኤርትራ በረሃ ሆኖ ይታገል የነበረው ዴምህት፣ በ2011 ዓ.ም ወርሃ መስከረም የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከሁለት ሺህ አምስት መቶ በላይ ሽምቅ ተዋጊዎቹን ይዞ ተመልሷል።

ሚሊዮን ሃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ