1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መኢአድ የታሰሩት አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ

ማክሰኞ፣ ጥር 16 2009

መኢአድ በደቡብ ኦሞ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ ከቅዳሜ አንስቶ የታሰሩት የመኢአድ 3 አመራሮችን ጨምሮ 13 አባላቱ እንዲፈቱ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት በጽሁፍ ጥያቄውን አቅርቧል ።

https://p.dw.com/p/2WKQZ
Logo Äthiopien Opposition Partei AEUP

Beri AA (Meiad ( AEUP ) says its leaders on custody - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ «የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት» በምህጻሩ መኢአድ በደቡብ ክልል ሰሞኑን የታሰሩት አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ ። የመኢአድ ሊቀመንበር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት በደቡብ ኦሞ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ ከቅዳሜ አንስቶ የታሰሩት የመኢአድ 3 አመራሮችን ጨምሮ 13 አባላቱ እንዲፈቱ ፓርቲያቸው ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት በጽሁፍ ጥያቄውን አቅርቧል ። መኢአድ እንደሚለው የታሰሩት ሦስቱ አመራሮች የፓርቲው የደቡብ ቀጣና ተጠሪዎቹ ናቸው ።  ሰዎቹ በቁጥጥር ስር ይገኙበታል የተባለውን የሳውላ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊዎች ለማነጋገር የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ