1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መዓዛ ብሩ በዶይቼ ቬለ

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2011

ዶቸ ቬለ በየዓመቱ የሚያዘጋጀዉ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ዘዴ መድረክ ወይም ጉባኤ (GMF) ዘንድሮ ለ12ኛ ዓመት እዚሕ ቦን ዉስጥ ተደርጓል። ባለፈዉ ሰኞ እና ማክሰኞ በተደረገዉ የዘንድሮዉ ጉባኤ ከመላዉ ዓለም የተወከሉ ወይም የተጋበዙ ጋዜጠኞች፣ የመገናኛ ዘዴ ባለቤቶች፤ ባለሙያዎች፤ ሳንቲስቶች እና አጥኚዎች ተካፍለዋል።

https://p.dw.com/p/3JTaU
Meaza Biru | Äthiopien | DW Amharisch | Bonn
ምስል DW

የሸገር FM ዋና ሥራ አስኪያጅ መዓዛ ብሩ

 ከኢትዮጵያ ዘጠኝ እንግዶች በጉባኤዉ መካፈላቸዉን አረጋግጠናል። የሰሞኑን ሥርጭታችንን የተከታተላችሁ እንደምታስታዉሱት በጉባኤዉ ከተካፈሉት መካከል የተወሰኑትን አነጋግረናል። ዛሬ ደግሞ ካነጋገርናቸዉ አንዷን በዚሕ በዜና መፅሔታችን ሁለተኛዋን በሳይንስ ዝግጅታችን እናቀርብላችኋላን። ከዜና መፅሕቷ እንግዳ ነዉ የምንጀምረዉ። የሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅና ብዙ ኢንተርቪዉ አድራጊ (ጠያቂ) ነች። መዓዛ ብሩ። ሸዋዬ ለገሠ ጠያቂዋን ጠይቃታለች። አብረን እንስማዉ። 

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ