1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መድረክ እና አባል ፓርቲዎቹ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 1 2002

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚሉት ግን የሁለቱ ፓርቲዎች አፈንጋጭ አቋም የመድረክ መሰነጣጠቅ አይደለም ባይ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/ODnt
ዶ/ር ነጋሶምስል DW

07 07 10

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ-ባጭሩ) ከሚያስተናብራቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለቱ ማፈንገጣቸዉን አስታወቀ።የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሠብሳቢ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንደገለፁት የሶማሌ ድርጅትና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) ፓርቲዎች መሪዎች ከመድረክ ደንብ፥ አሠራርና ስምምነት ጋር የሚቃረን ምግባር እየፈፀሙ ነዉ።ይሁንና መድረክ ሁለቱን ፓርቲዎች እስካሁን በይፋ ከአባልነት አላስወገደም።ነጋሽ መሐመድ ዶክተር ነጋሶን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅሯል።

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ።ካለፈዉ የካቲት ወዲሕ ግን የሥምንቱ ፓርቲዎች መሪዎች ሥራና እንቅስቃሴ የስምንት መሪዎች አይነት አልሆነም።መድረክም ከስምት ፓርቲዎች ጥምረት ይልቅ የስድስት ፓርቲዎች ያክል ነበር።ምክንያት፣-እንደገና ዶክተር ነጋሶ

ከየካቲቱ ጉባኤና መግለጫ በሕዋላ የሁለቱ ፓርቲዎች መሪዎች በመድረክ ዉስጥ ሥላላቸዉ ዉክልና ሲወዛገቡ ነበር።ዉዝግቡ ለተቀሩት የመድረክ አባል ፓርቲዎች መሪዎች አልተሸሸገም ነበር።መፍትሔ ግን አልተገኘም።ዉስጣዊ ይመስል የነበረዉ የሁለቱ ፓርቲዎች ዉዝግብ አድጎ-የሁለቱ ፓርቲዎችና የተቀረዉ የመድረክ አካልም ሆነ።

ሁለቱ ፓርቲዎች ከመድረክ መዉጣታቸዉን ባያስታወቁም።በግንቦቱ ምርጫና ከምርጫዉ በሕዋላ የሚሉ የሚያደርጉት ግን ከመድረክ የጋራ አቋምና እምነት የሚቃረን ነዉ-ይላሉ ዶክተር ነጋሶ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም ተቃዋሚዎች አንድነታቸዉን ባወጁ ማግሥት መከፋፈላቸዉን ማስተዋል በርግጥ እንግዳ አይደለም።አሁን መድረክን የገጠመዉም ያ ከዚሕ ቀደም የሚታወቀዉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሰነጣጠቅ አይነት መምሰሉ አልቀረም።ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚሉት ግን የሁለቱ ፓርቲዎች አፈንጋጭ አቋም የመድረክ መሰነጣጠቅ አይደለም ባይ ናቸዉ።እንዲያዉም በተቃራኒዉ ይላሉ ዶክተር ነጋሶ የመድረክ አባል ፓርቲዎች ጥምረታቸዉን ለማጠናከር እየተወያዩ ነዉ።

መድረክ ባለፈዉ ግንቦት በተደረገዉ ምርጫ ከገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዲግ ቀጥሎ ከፍተኛዉ ድምፅ ያገኘ ጥምረት ነዉ።ይሁንና ድርጅቱ የምርጫዉን ዉጤት ዉድቅ አድርጎ ድጋሚ ምርጫ እንዲደረግ ፍርድ ቤት እየተሟገተ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ