1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መድረክ ከኢህአዴግ ጋር የሁለትዮሽ ዉይይትን ጠየቀ

ዓርብ፣ መጋቢት 22 2009

ኢህአዴግ ከመድረክ ጋር የሁለትዮሽ ድርድር በአስቸኳይ እንዲጀምር መድረክ አሳሰበ። ለሃገራችን ፖለቲካዊ ችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ ለማግኘት ኢህአዴግ ከሃቀኛ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ሊያካሂድ ይገባል፤ ይላል መድረክ ዛሬ ባስነበበዉ የጽሑፍ መግለጫ ርዕስ። ፓርቲዉ ሊደራደርባቸዉ የሚያስፈልጉ አስቸኳይ ጉዳዮች አሉም ብሎአል።

https://p.dw.com/p/2aSTs
Äthiopien Pressekonferenz
ምስል DW/G. Tedla

Ber. A.A (MEDREK will nur bilaterale Verhandlungen mit EPRDF) - MP3-Stereo

የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ጨምሮ የመድረክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መድረክ ላቀረባቸዉ ጥያቄዎች ፈጣንና ተጨባጭ ዉጤቶችን ሊያስገኝ የሚችለዉ የሁለትዮሽ ድርድር ሲካሄድ ነዉ ብለዋል።  


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር


አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ