1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ የሚያሻዉ የስደት አባዜ

እሑድ፣ ጥቅምት 28 2008

በጎርጎሪዮሳዊዉ 2013 ዓ,ም የሳዉድ አረቢያ መንግሥት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ በግዛቱ የሚገኙ የዉጭ ሃገራት ዜጎችን ሲያባርር፤ ለከፍተኛ ችግር ከተጋለጡት መካከል ኢትዮጵያዉያን ግንባር ቀደሞቹ ነበሩ።

https://p.dw.com/p/1H1LS
Symbolbild Flüchtlinge Mittelmeer EU
ምስል Reuters/I. Zitouny

መፍትሄ የሚያሻዉ የስደት አባዜ

በወቅቱ ወደሀገራቸዉ የተባረሩ ኢትዮጵያንን በማነጋገር የተዘጋጁ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህን ወገኖች ለስደት ካበቁ ምክንያቶች በዋነኛነት የተሻለ ኑሮ ፍለጋ የሚለዉ ሚዛን ይደፋል። በገዛ ሀገር ያልተገኘዉን የተሻለ ኑሮ በማያዉቁት ሌላ ስፍራ ለማግኘት ሲባልም ሕይወትን እስከማጣት እና ለተለያዩ ጥቃቶች መጋለጡ በየጊዜዉ የሚሰማ የብዙዎች ገጠመኝ ነዉ። አሁንም ግን የተሰዳጁ መጠን አለመቀነሱ እያነጋገረ ነዉ። ጉዳዩን የሚከታተሉና ስደተኞችን በተመለከተ የሚሠሩ ድርጅቶች «የመሰደድ ባህል» እያሉ መጥራት የጀመሩት ይህ የስደት አባዜ እንዴት ሊገታ ይችላል? ዶቼ ቬለ ለዚህ ሳምንት ዉይይት ያካሄደበት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። ከድምጽ ዘገባዉ ሙሉዉን ዉይይት ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ