1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ ያላገኘዉ የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉዝግብ

እሑድ፣ ኅዳር 12 2008

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጠለዉ ቁርቁስና፣ ፖለቲካዊ ዉዝግብ አሁን ደግሞ በስፖርቱ ላይ ጫናዉን ያሳረፈ መስሏል። ኢትዮጵያ ከሕዳር 11 ጀምሮ ለ 15 ቀናት በምታስተናግደዉ የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገሮች «ሴካፋ» የእግር ኳስ ሻምፒዮናን ኤርትራ እንዳትካፈል ኢትዮጵያ አግዳለች ሲል አሶሺየትድ ፕረስ ያወጣዉን ዘገባ ተከትሎ፤

https://p.dw.com/p/1HAGQ
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

[No title]

ኢትዮጵያ ዘገባዉን ሃሰት ስትል ኤርትራ በበኩልዋ ለዉድድሩ ወደ ኢትዮጵያ እንደማትሄድ አስታዉቃለች። በመሠረቱ ስፖርት በሕዝቦች መካከል ያሉ የቀለም፤ የፖለቲካ፤ የጾታ፤ የእድሜ ወዘተ ልዩነቶችና አመለካከቶችን ለማስወገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ስፖርት ለወዳጅነት የሚባለዉም ለዚህ ነዉ። የሁለቱ ሀገራት እሰጣ አገባ በስፖርት እንቅስቃሴዉ ላይ ብሎም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለዉን ልዩነት እያሰፋዉ መሆኑ እሙን ነዉ። መፍትሄ ያጣዉን የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉዝግብ በተመመለከተ በአዘጋጀነዉ ዉይይት ላይ፤ ከኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ ተንታኝ ተባባሪ ፕሮፊሰር መድሕኔ ታደሰ፤ በብሪታንያ በሚኖሩ ኤርትራዉያን ማኅበረሰብ ዘንድ በስፖርት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋጽኦ በማድረጋቸዉ የሚታወቁት አቶ አሉላ አብርሃ፤ እንዲሁም ከሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን የወዳጅነት መድረክ ተጣማሪ ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ አንለይ ተካፍለዋል።

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ