1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መፍትሄ ያላገኘው በሊቢያ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2005

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገን ጠያቂዎች በሊቢያ ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ አንዳንድ ስልክ ደውለው የገለፁልን ኢትዮጵያውያን አስታወቁ። «ስለኛ ተጠያቂ አካል የሆነ መፍትሄ እንዲፈልግልን እና እንዲያነጋግረን» ጠይቁልን ሲሉም ለዶይቸቬለ ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/16OIO
"Free Libya" Detention Camp in Bengazi, Libyen (Juni 2012; Credit Sara Prestiani). "Free Libya" ist ein Durchgangslager***via Joanna Impey
ምስል Sara Prestiani

ስደተኞቹ ያሉበት የመጠለያ ጣቢያ ጠባቂዎች እንዳያዩዋቸው እየተደበቁ ነበር በስልክ ያነጋገሩን። ከተለያዩ አገር ነው በርሃ አቋርጠው ሊቢያ የገቡት። ቀይ ጨረቃ ከገቡ ከስድስት ወር እስከ ዘጠኝ ወር ሆኗቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ከአምስት ሀገራት የመጣን ስደተኞች በግምት 300 እንሆናለን ይላል ያናገረን ስሙ እንዳይገለጽ የጠየቀን ስደተኛ። በመጠሊያ ስላሉ ችግሮች መረጃ እንዳላቸው ሊቢያ ያለውን የUNHCR ተጠሪ ኤማኑኤል ጂኛክን ጠይቀናል። የሁለቱንም አስተያየት ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ