1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙምባይ-ታላቋ ከተማ

ሐሙስ፣ መስከረም 13 2003

ሙምባይ ታላቁን ቦታ የምትይዝ የታዋቂቆች እና የተከበሩ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ናት። በሙምባይ ግማሹ የከተማዋ ነዋሪ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት የለዉም፣ የሚኖረዉም

https://p.dw.com/p/PJTz
ምስል DW

ሙባይ በህንድ የማሃራሸትራ ክፍለ ግዛት ዋና ከተማ ሲሆን በዚሁ በሙባይ ከተማ ዉስጥ የሚገኘዉ ባይኩላ ክፍለ ከተማ በደቡብ ሙባይ አሉ ከሚባሉት ከተሞች ሁሉ ረጅም እድሜ ያለዉ መንደር ነዉ። በባይኩላ ክፍለ ከተማ ጎዳና በቤት መኪና ጩኸት በህዝብ ማመላለሻ አዉቶቡስ እና በህዝብ ተጨናንቆ ይታያል። የሰላሳ ሶዎስት አመቱ ደራሲ አልታፍ ታሪዋላ እንኳን ደህና መጣህ ብሎ ቢቀበለኝም በዚህ ክፍለ ከተማ እንደማንቆይና፣ እሱ ከዚህ ከተጨናነቀ ከተማ ወጣ ብሎ እፎይ ወደ የሚልበት እና ዳግም ጉልበት ወደ ሚሰበስብበት ሰፈር እንደሚወስደኝ ነበር የገለጸልኝ። ይህ የምንሄድበት ቦታ የጆን ባቢስታ ጋርድን ይባላል። ከባይኩላ መንደር ሁለት ኪሎ ሜትር ግድም ርቆ የሚገኝ በአንድ ኮረብታ ላይ ያለ አረንጓዴያማ ስፍራ ነዉ።

ሙባይ የትዉልድ ቦታዪ መኖርያ ናት በማለት አልታፍ ታሪዋላ ትረካዉን ይጀምራል። ሙባይ ከተማ ከልጅነት እስከዉቀት ግዜዉን ያሳለፈበት የህይወት ዉጣ ዉረድን ያየበት ታላቅ ማስታወሻዉ ናት። በዚህም ይላል ደራሲ አልታፍ በእዝች አለም ላይ አንድ ምርጥ ቦታ አለ ቢባል፣ ሙባይ በታላቁን ቦታ የምትይዝ የታዋቂቆች እና የተከበሩ ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ናት። በሙባይ ግማሹ የከተማዋ ነዋሪ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት የለዉም፣ የሚኖረዉም በድህነት በቆርቆሮ በተሰራ ቤት ዉስጥ ነዉ። በሌላ በኩል ደግሞ ሁለት መቶ ያህል ሃብታሞች የሚገለገሉበት የሰዉነት ቅርጽ መጠበቅያ ጣብያም ይገኛል። በአጠቃላይ በህንድ ዉስጥ ካሉ ከተሞች ሁሉ ሃብታሟ ሙባይ ከተማ ስትሆን በጣም ቆሻሻ ከተማም ናት። የሙባይ እያንዳንዱ ነዋሪ በቀን ሁለት ፓኮ ሲጋራ የሚያጨስ ያህል የከተማዋ ከባቢ አየር ቆሻሻ ነዉ፣ ሲል የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት ስለ ሙባይ የከባቢ አየር መበከል ይገልጻል።

ታድያ ሙባይ ከተማ ራስዋ አንድ ልብ ወለድ አይደለች? ስል ደራሲ አልታፍ ታሪዋላን ጠየኩት። አዎ ለዝያዉም ከአንድ ድንቅ ደራሲ የተጻፈች፣ በጣም አጓጊ ግን ጠመዝማዛና ከባድ ተደርጋ የተደረሰች ሲል መለሰልኝ። ከተማዋ ለደራሲዉ ብዙ አስደናቂ ታሪኮች ያሉባት፣ ገና ብዙ ታሪኮችዋ ደግሞ የማይታወቁ ሆና ያገኛታል። ከዝያም ደራሲ አልታፍ በመቀጠል የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ለትምህርት ስለሄደባት ስለ ኔዉ ዪርክ መተረኩን ቀጠለ። አልታፍ ታሪዋላ አስራ ስምንት አመት እንደሞላዉ በዪንቨርስቲ የኢኮነሚ ትምህርቱን ለመከታተል ወደ ኒዮርክ ሄዶ ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ ትዉልድ ከተማዉ ወደ ሙንባይ ተመልሶአል። በኒዮርክ ሳለሁ ይላል አልታፍ በርካታ የዉጭ ዜጎች ያላዩትን ማየት ችያለሁ። በቀን የተለያዩ ሶስት ስራዎች እሰራ ነበር። የምኖርበትን የቤት ክራይ መክፈል እድንችል ደግሞ አንዳንድ ግዜ በቀን ሳልበላ የምዉልበት ግዜ ነበር። ይህ ሁሉ ታድያ በህልም የማዉቀዉን ብልጭልጩን የአሜሪካዉያን የኑሮ ዘዴ ምንም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ አድርጎልኛል።

Stadtteil Malad von Mumbai in Indien Flash-Galerie
ሐብታምና ደሐምስል DW

የተስፋ ከተማ

ታዋቂዉ ህንዳዊ ደራሲ የአልታፍ የስራ ባልደረባ የሆነዉ ኪራን ናጋርካር ሙባይ ሱስ የምታስይዝ ከተማ ሲል ስለሙባይ ምንነት ፍች ይሰጣል። በድርሰቱም ሙባይ ሰዉ በሱስ እንዳይያዝ ሳይሆን እስከ መጨረሻዉ በሱስዋ ተይዞ የሚያልፍባት ከተማ ሲል ስለ ሙባይ ጽፎአል። ሙባይን ከገለጸበት ከዚህ አይነት ከባድ አገላለጾቹ ጋር ነዉ ዛሪ የምቆየዉ። በአጠቃላይ ለደራሲዉ ሙባይ ተስፋ የሚያገኝበት ከተማዉ ነች።


አልታፍ ታሪዋላ ከእናቱ ከባለቤቱ እና ከአስር ወር ልጁ ጋር በባይኩላ ዉስጥ በሚገኝ አንድ ረጅም ህንጻ ዉስጥ ባለ አነስተኛ መኖርያ ቤት ዉስጥ ነዉ የሚኖረዉ። አልታፍ አክራሪ ካል ሆኑ የእስልምና ሃይምኖት ተከታይ ወላጆቹ ጋር ነዉ ያደገዉ። በሙባይ ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከድሮ ጀምሮ የሚከተሉት ኢማም አጋ ካንን ነዉ። ሙባይ የተለያየ ባህል ያለዉ ህዝብ የሚኖርባት ከተማም ነች። ሆኖም ግን በእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እና ሃይማኖቱ ላይ የተሳሳተ አመለካከት እና ልማድ አለ ሲል አልታፍ ያምናል። በሙባይ እ.አ 1992 አ.ም እና እ.አ1993 አ.ም በሂንዱስ እምነት ተከታዪች እና በሙስሊሞች መካከል በተፈጠረ ከባድ ግጭት 900 ያህል ህዝብ ህይወቱን አጥቶአል። ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ሙስሊሞች ነበሩ።


መቃብር ቤት

የነበርንበት ፓርክ ለቀን ወደ ከተማ ተመልሰን። በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በሙባይ ስራ ፍለጋ እድሉን ለመሞከር ይመጣል። ታድያ አንዳንዶች ሲቀናቸዉ ሌሎች ደግሞ እድል ሳያጋጥማቸዉ ይቀራል። ተመጣጣኝ የኑሮ ገቢ የነበረዉ እድሉን ለመሞከር በሙባይ የመጣ በሞባይ በአራት ግርግዳ ዉስጥ መኖሩ ቀላል እንደማይሆንለት አልታፍ ይገልጻል። በሙባይ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ጠንቅቆ ያዉቃል። አልታፍ ራሱ በሙባይ በአንድ የመኖርያ መንደር ቤት ለመግዛት ፍለጋ ከያዘ ወራቶች እንደተቆጠሩ እና እስካሁን እንዳላገኘ በንዴት ይገልጻል። በመቀጠል ሰሃ ሃሰን አሊ ሙክባራ ወደ ተሰኘ አንድ የሙንባይ መንደር መጣን። በዚህ መንደር አንድ ትልቅ ከነጭ እምነበረድ የተሰራ የመቃብር ቤት በስተቀር ሁሉ ነገር ረጭ ያለ ነዉ። በዚህም ጫጫታ እና ሞቅ ባለዉ በሙንባይ ከተማ መሃል ከባድ ጸጥታ የሰፈነበት ቦታ ሰሃ ሃሰን አሊ ሙክባራ ብቻ ይሆናል። ታድያ ከሁሉም ከሁሉም ደራሲ አልታፍን የሚያስደስተዉ በዚህ መቃብር ቤት ደረጃ ላይ ሆኖ በኤሌክትሮኒክስ የማስታወሻ ደብተሩ ገጠመኞቹን ማስፈር ነዉ።

Indien, Mumbai, Frauen waschen Wäsche im Slum
ልብስ አጠባ-በአዉራ ጎዳናምስል AP

“በሙባይ ሁሉ ነገር በታቀደበት ግዜ ነዉ የሚፈጸመዉ። እንደኔ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ አራት ሰአት ይላል። ደጁ ግን ለአይን ያዝ ጨለም ያለ ይመስላል። የመኪናዪ መስኮትም ጠቁሮአል። ጭንቅላቴን በትንሹ ወደ ቀኝ መለስ ባደርግ፣ ያቺን የተጨናነቀች የቆሸሸች ጭስ የምትተፋ ከተማ አያለሁ። እኔ እዚህ ላይ የልቦለድ፣ ታሪክ ሰዉ አይደለሁም። የመኪናዪ መስታወት በጥቁር ቆሻሻ አልፎ አልፎ በመሸፈኑም የአንተን ሙንባይ አጥርተህ እንዳትመለከታት በከፊል ጋርዶታል”


አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ