1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙስና በቱርክ

ሐሙስ፣ ጥር 1 2006

ቱርክ ውስጥ የተከሰተውን ከፍተኛ የሙስና ቅሌት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሠራተኞች ከስራ ገበታቸው ተሰናብተዋል አለያም ወደሌላ ቦታ ተዛውረዋል። የሙስና ቅሌቱ ቱርክ ውስጥ ሌሎች አነጋጋሪ ነገሮችም ይዞ ብቅ ብሏል።

https://p.dw.com/p/1AoIW
ሙስና በቱርክምስል Ozan Kose/AFP/Getty Images

በቱርክ ሀገር በስልጣን በመባለግና በሙስና ተከሰው በርካታ ሰዎች ከስልጣናቸው ከተባረሩ ወዲህ በሀገሪቱ የኃይል አሰላለፍ ወዴት እንዳጋደለ መገመቱ አስቸጋሪ ሆኗል። የፖሊስ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖችና አዛዦችን እንዲሁም ሚንስትሮችን ጨምሮ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ባለስልጣናት ቱርክ ውስጥ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል። በሙስና ጽዳት ዘመቻው ፊታውራሪ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሀገሪቱ አቃቤያነ ሕጎችና ዳኞችም ከስራቸው ተባረዋል። የበርልኒ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከቱርክ ውጪ በብዙ መቶ ሺህ ቱርኮች በሚኖሩባት የበርሊንከተማ ተዘዋውሮ የቱርክ ተወላጆችን አነጋግሯል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ