1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙስና በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ግንቦት 10 2010

የኤኮኖሚ ባለሞያዎች እንደሚሉት ሙስና የኢትዮጵያን እድገት ከሚያጓትቱት ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ነው። ዶቼቬለ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ምሁራን በተለያዬ መንገድ የሚፈፀመው ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ እያደገ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/2xxmF
Hände übergeben Euros
ምስል picture-alliance/U.Baumgarten

ሙስና በኢትዮጵያ

የሀገራትን የሙስና ደረጃ የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት በጎርጎሮሳዊው 2017 ኢትዮጵያን በሙስና  ከ180 ሀገራት፣117ተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል። የኤኮኖሚ ባለሞያዎች እንደሚሉት ሙስና የሀገሪቱን እድገት ከሚያጓትቱት ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ነው። ዶቼቬለ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ምሁራን በተለያዬ መንገድ የሚፈፀመው ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ እያደገ ነው ሲሉ አስረድተዋል። በሀገሪቱ ሙስና የህዝባዊ አመጽ መንስኤ እንደነበረም የቅርብ ጊዜዎቹን ተቃውሞዎች ምሳሌ አድርገው ተናግረዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል። 
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ