1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙባይ የሥልጣኔ-ሥይጣኔ ከተማ

ሰኞ፣ ኅዳር 22 2001

ሽብር ከየዘመኑ ትዉልድ አዕምሮ የሚያጠፋበት ብልሐት-ዘመን እንደራቀ የሽብር ጥቃቱ አይነት እንደተለዋወጠ ትዉልድ ሔዶ ትዉልድ የመተካቱ ኡደት እንጂ ግራዉ---

https://p.dw.com/p/G701
ሽብርምስል AP

የጉጅራቱ ሱልጣን ባሐዱር ሻሕ የግዛታቸዉን አዋሳኝ ከተቆጣጠሩት ከፖርቱጋሎች ጋር የተሻረኩት ክንዳቸዉ እየፈረጠመ፥ ግዛታቸዉ እየሰፋ፥ ደጋፊያቸዉ እየበረከተ ከመጣዉ ከሙጋል ሥርወ-መንግሥት መስራቾች ጥቃት ለመዳን ዘዴ ብለዉት ነበር።ያቺን ዉብ የባሕር ዳርቻ ከተማቸዉን ለአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎች መስጠት ግን ግድ ነበረባቸዉ።ሰጡ።1534።ሡልጣኑ አዲስ ወዳጆቻቸዉን ለመጎብኘት ከድሮ ከተማቸዉ አጠገብ መሕልቋን ከጣለችዉ መርከብ ሲሳፈሩ በወዳጆቻቸዉ ተገደሉ።1537።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የማራቲዮቹ እናት አማልዕክት፥ መሪዋ በወዳጅ-ጠላቶቻቸዉ የመገደላቸዉን ጉድ ታሪክ አራት መቶ ሰባኛ አመት ለመዘከር ወራት ሥታሰላ በቀደም በሽብር ተናወጠች።በደም ጨቀየች።ሙባ፥ መሐ-አምባ፥ ሙባይ-ወይም ቦምቤይ።