1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙዚቀኛ መና ሙሉጌታ

ዓርብ፣ ሰኔ 15 2004

መና ሙሉጌታ ትባላለች። ዛሬ የራሷን አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎች ይዛ በወጣቶች አለም እንግዳ ናት።

https://p.dw.com/p/15JvK
Sängerin, Menna Mulugeta. Copyright: Menna Mulugeta Juni, 2012
«ራይንላንድ ፋልስ» ተብላ በምትጠራ የጀርመን ክፍለ ግዛት በተዘጋጀ የዘፈን ውድድር ላይ መና ተወዳድራ አንደኛ የወጣችው ገና የ14 አመት ልጅ ሳለች ነው።ምስል Menna Mulugeta
Menna Mulugeta CD Cover
የመና ሙሉጌታ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበምምስል Menna Mulugeta

መና ተወልዳ ያደገችው እዚሁ ጀርመን አገር ነው። ሙዚቃ መጫወት ትወዳለች። ይህንንም ችሎታዋን አዳብራ ስራዎቿን በCD አሳትማ መሸጥ ጀምራለች። መና ማዜም የጀመረችው በልጅነቷ ነው።

«ራይንላንድ ፋልስ» ተብላ በምትጠራ የጀርመን ክፍለ ግዛት በተዘጋጀ የዘፈን ውድድር ላይ ተወዳድራ መና አንደኛ የወጣችው ገና የ14 አመት ልጅ ሳለች ነው። የኪነ ጥበብ ሰዎች ዘፈኖችን አስመስላ መጫወት ብቻ ሳይሆን የራሷን ስራዎችንም ዛሬ ለገበያ አብቅታለች። መና የአርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ዜማን በስራዎቿ ውስጥ አካታለች። ምን እንዳነሳሳት ገልፃልናለች።

«በብዛት የፃፍኳቸው ግጥሞች ከግል ህይወቴ ጋ ይገናኛል።» ትላለች መና ።ብዙውን ጊዜ፤ በቤተ ክርስትያን፤ በሙዚቃ ትርዒቶች፣ ድግሶች እንዲሁም በሌሎች ትላልቅ ዝግጅቶች ላይ እየተገኘች ታዜማለች። እንደገለፀችልን ይህንንም ለብዙ አመታት ከትምህርቷ ጎን ለጎን ለማራመድ ችላለች። የወደፊት አላማዋም በሙዚቃው አለም መቆየት ነው። ስለ ግል ስራዎቿ ያጫወተትንን ማድመጥ ይችላሉ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ