1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙጋቤ ቃለ መሐላ ፈጸሙ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2005

የ89 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ በዛሬዉ ዕለት ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሆነዉ ቃለ መሃላ ፈጸሙ።

https://p.dw.com/p/19Unw
ምስል Getty Images/Afp/Alexander Joe

ሙጋቤ ባለፈዉ ሐምሌ ወር ማለቂ ላይ በተካሄደዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ 61 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸዉን የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት ነዉ ያጸደቀዉ። ተፎካካሪያቸዉ ጠቅላይ ሚኒስር ሞርጋን ቻንጊራይ ዉጤቱ ተጭበርብሯል ቢሉም ያንን የሚደግፍ መረጃ ለማግኘት ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ አልተባበረኝምና ፍትህ አላገኝም በማለት ቀደም ብለዉ ክሱን ማቋረጣቸዉን አመልክተዉ ነበር። ከፍርድ ቤቱ ዉሳኔ በኋላ ዛሬ ሙጋቤ ቃለ መሃላ ሲፈጽሙም ብሪታኒያ እሳቸዉ ዳግም መመረጥ በገለልተኛ ወገን አቤቱታዉ ሳይጣራ ተአማኒነት ይጎድለዋል ብላለች። ላለፉት 33ዓመታት የዚምባቡዌ መሪ የነበሩት ሙጋቤ በነቃፊና ደጋፊዎቻቸዉ አይን እንዴት ይታያሉ? ለምንስ ስልጣን መልቀቅ አይፈልጉም? ሎንዶን የሚገኘዉን ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህን አንዳንድ ነጥቦች በማንሳት ቀደም ብዬ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

ድልነሳ ጌታነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ