1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማህበራዊ የጤና መድን አገልግሎት

እሑድ፣ ጥር 7 2009

የጤና አገልግሎት ሽፋን መስፋፋት ለአገሪቱ የተቀላጠፈ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያ ካለፉት ሰባት ዓመታት ወዲህ ማኅበራዊ የጤና መድን አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ አዋጅ አውጥታለች።

https://p.dw.com/p/2Vn8X
Arzt Rezept
ምስል fotolia/Bernd_Leitner

ማህበራዊ የጤና መድን ዋስትና የገጠመው ችግር

በዚሁ አዋጅ 690/2002  መሰረት፣ በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ ሶስት ዓይነት የጤና መድን ዋስትና(ኢንሹራንስ) አገልግሎት ስርዓት አሉ።  ከሶስቱ አንዱ የሆነው ሁሉንም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሰራተኞችን እና የጡረታ ባለመብቶችንም እንዲያቅፍ የተዘጋጀው ማህበራዊ የጤና መድን ሽፋን ነው። ሌሎቹ የግል እና የማህበረሰባዊ የጤና መድን አገልግሎቶች ናቸው።  በኢትዮጵያ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ማኅበራዊ የጤና መድን አገልግሎት እክል እንዳጋጠሙት ተነግሮዋል። ይኸው በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ሊጀመር የታሰበው እና ግዴታን መሰረት ያደረገው ማኅበራዊ የጤና መድን ሥርዓት ከሁለት ዓመት በፊት ነበር በስራ ላይ መዋል የነበረበት። የዛሬው ውይይት አገልግሎቱ ያልተጀመረበትን ምክንያት እና የአገልግሎቱ የወደፊት ይዞታን ይመለከታል። 

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ