1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማንዴላ «ላይመጡ ሔዱ»

ዓርብ፣ ኅዳር 27 2006
https://p.dw.com/p/1AU4E
Eröffnung des Nelson Mandela Centre for Memory in Johannesburg, Südafrika
ምስል Reuters

የደቡብ አፍሪቃ የነፃነት ታጋይና የቀድሞ ፕሬዝዳት ኔልሳን ማንዴላ በመሞታቸዉ ከዓለም የሚወጣዉ የሐዘን መግለጫ እንደቀጠለ ነዉ።የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዝዳት ጄኮብ ዙማ «ሐገራችን ታላቅ ልጅዋን አጣች፣ ሕዝባችን አባቱን አጣ» ብለዋል።ከማንዴላ የዓለም ታላቅ የሠላም ሽልማት ኖቤል የተጋሩት የመጨረሻዉ የደቡብ አፍሪቃ ነጭ ፕሬዝዳት ፍሬድሪክ ደ ክላርክ ከማንዴላ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም አብሬ በመስራቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ብለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ እንዳሉት ደግሞ ኔልሰን አብነታዊ ምግባር ባይኖር ኖሮ የራሴን ሕይወት በዚሕ መንገድ ማሰብ አልችልም ነበር።የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸዉ «በዘመናዊዉ የዓለም ታሪክ ካታላላቅ ፖለቲከኞች አንዱ» በማለት አድንቀዋቸዋል።ሌሎችም እንዲሁ።ማንዴላ ደቡብ አፍሪቃን ከዘር መድሎ ሥርዓት ለማላቀቅ ግማሽ እድሜያቸዉን የታገሉ፥ ሃያ-ሰባት ዓመታት የታሠሩ፥ በስተመጨረሻም በሁሉን ዘር አቀፍ ምርጫ ሥልጣን የያዙ የመጀመሪያዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳት ነበሩ።ማንዴላ ያረፉት ትናንት ማታ ነዉ።95 ዓመታቸዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ