ትምህርት
ማካካሻ ትምሕርት ለተፈናቃዮች
ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2011ማስታወቂያ
በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ግጭትና ጥቃትን ሸሽተዉ ከቤት ንብረታቸዉ በመፈናቀላቸዉ ትምሕርት ላቆረጡ 300,000 የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ዘንድሮ ክረምት የማካካሻ ትምሕርት እንደሚሰጥ ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ።የሚንስቴሩ ባለስልጣናት እንደሚሉት ተፈናቃይ ተማሪዎችን ለማስተማር 6000 መደበኛ አስተማሪዎችና 6000 በጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአካባቢዉ ይዘምታሉ።ትምሕርት ሚኒስቴር ያቀደዉ የማካካሻ ትምሕርት እንዲሳካ የለጋሽ ወገኖችን ድጋፍ ጠይቋልም።ኢትዮጵያ ዉስጥ አምናና ዘንድሮ በየአካባቢዉ በተደረጉ ግጭቶችና በደረሱ ጥቃቶች በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለዉ በትንሽ ግምት ከ2.5 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተፈናቅሏል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ