1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማድሪድ፣ ጥቃትና የፍርድ ዉሳኔ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 21 2000

የማድሪድ ፍርድ ቤት በአዉሮፓዉያኑ 2004 ዓ.ም የሽብር ጥቃት አድርሰዋል ባላቸዉ ሶስት ሰዎች ላይ 42 ሺህ ዓመት እስራት ፈረደ። ተከሳሾቹ ስፓኝ ላይ በተጠቀሰዉ ዓመት አድርሰዉታል በባለዉ ጥቃት የ191 ሰዎችን ህይወት ሲጠፋ ወደ2000 የሚደርሱት ደግሞ ለጉዳት ተዳርገዋል።

https://p.dw.com/p/E87X
ሞሮኳዊዉ ጀማል
ሞሮኳዊዉ ጀማልምስል AP

እንደአዉሮፓዉያኑ አቆጣጠር በመጋቢት 2004ዓ.ም የህዝብ ማመላለሻ በሆነዉ ባቡር ላይ ጥቃቱ ሲደርስ ሰራተኛ ወደስራዉ የሚጣደፍበት ሰዓት ነበር። በወቅቱ በስፓን ስልጣን ላይ የነበረዉ ከማዕከላዊነት ይበልጥ ቀኝ ዘመም ታዋቂ ፓርቲ ወዲያዉ የባስክ ክፍለ ሀገርን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሰዉ በምህፃሩ ETA የተሰኘዉን ቡድን ተጠያቂ ነዉ አለ።

በሶስተኛ ቀን በምርጫ ተሸንፎ የተሰናበዉ ይህ ፓርቲ እስከመጨረሻዉ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ETA እጁ አለበት ማለቱን አላቋረጠም። በወቅቱ ስፓኝ ወታደሮቿን ከአሜሪካ ወታደሮች ጋ ወደኢራቅ በማዝመቷ የጆሴ ማሪያ አዝናር መንግስት ዉጥረት ነበረበት። ዉጤቱም በምርጫዉ ተሸንፎ ከስልጣን ለመሰናበት ዳረገዉ። በተከሳሾቹ ላይ የፍርድ ዉሳኔዉን የሰጡት ዳኛ ጃቪየት ጎሜዝ ቤርሙድዝ ለይተዉ እንዳስረዱት የተባለዉ ቡድን ጥቃቱን በመጠንሰሱ ረገድ መሳተፉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አልተገኘም።


«የመረጃዉ እዉነታና ተቀባይነት እንደሚያሳየዉ፤ ፍርድቤቱ በሚገባ እንዳረጋገጠዉና በተጠየቃዊ ሂደት ነገሩን እንደመረመረዉና ከልምድም ተነስቶ የደረሰበት ዉሳኔ እንደወትሮዉ ሁሉ በጥንቃቄ በተካሄደ ምርመራ በመሆኑ ስህተት የለበትም።»


ጨምረዉ እንደባራሩትም በባቡሩ የጀርባ እቃ መጫኛ ስፍራ የተከተቱት ፈንጆዎች የባስክ የሽብር ጥቃት አድራሾች የሚጠቀሙበት ዓይነት አይደለም። ንጥረ ነገሩ የመጣዉ በሰሜናዊ የስፓኝ ግዛት አስቱሪያስ ከሚገኘዉ የኮንቺታ የማዕድን ማዉጫ ስፍራ ነዉ። ከጥቃቱ ጋ በተገናኘ ተጠረጠሩ ሰባት ሰዎች ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሶስት ሳምንት በኋላ ፖሊስ መኖሪያ ህንፃቸዉን ሲከብ ራሳቸዉን ገድለዋል።

ሆኖም እነሱን ጨምሮ ከዚሁ ጥቃት ጋ በተገናኘ በጥቁ 29ሰዎች ናቸዉ ክስ የተመሰተባቸዉ። 21ዱ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ከእነሱ መካከል ሶስቱ የ42 ሺህ ዓመት እስራት ተበይኖባቸዋል። ቀሪዎቹ 18 ንቱ ደግሞ ከሶስት እስከ 12 ዓመታት ተፈርዶባቸዋል። 42 ሺህ ዓመታት ከተፈረደባቸዉ መካከል አንደኛዉና ጀማል ዙዋጉም የተባለዉ የተፈረደበት ፈንጂዎቹን ቢያንስ በአንደኛዉ ባቡር ዉስጥ በማስቀመጡ ሲሆን ሌላኛዉ ግብራበሩ ደግሞ ፈንጆቹን ከሌላ ስፍራ ወደማድሪድ በማጓጓዝ ነዉ። ሶስተኛዉና ሱሬዝ ትራሾራስ የተባለዉ ተከሳሽ ቀድሞ ቀደም ሲል በተጠቀሰዉ የማዕድን ማዉጫ ይሰራ እንደነበና ፈንጁዎቹ ለሽብር ተግባር እንደሚዉሉ እያወቀ ሆን ብሎ በመስረቅ ለጥቃት አድራሾቹ መስጠቱ በፍርድ ቤቱ ተረጋግጦበታል።

ሶስት ዓመት የፈጀዉ የፍርድ ሂደትም ዉሳኔዉን በሺዎች በሚቆጠሩ ዓመታት ፍርድ ሲያጠናቅቅ ዳኛዉ የሞሮኳዊዉ ዞዋጉምን በድርጊቱ መሳተፍ ሲያወግዙ ጣሊያን ዉጥ በእስር ላይ የሚገኘዉ ግብፃዊ ራቢ ዖስማን ሰይድ አህመድ በጥቃቱ እጁ እንደሌለ አሳዉቃል፤


«ጀማል ዞዋጉምን የምናወግዘዉ የሽብር ተግባር በሚፈፅም ቡድን ዉስጥ አባል ሆኖ በመገኘቱ ነዉ፤ በአንፃሩ ራቢ ዖስማን ኤል ሰይድ በሁሉም አቅጣጫ ከዚህ ጥቃት ጋ በተገናኘ ተከሶበት ከነበረዉ ሁሉ ነፃ መሆኑን እናሳዉቃለን።»


በጥቃቱ ቤተሰቦቻቸዉንና ወገኖቸዉን ያጡትም ሆኑ ጉዳት የደረሰባቸዉ ቤተሰቦች ግን በዉሳኔዉ አልተደሰቱም። በስፓኝ ህግ የተፈፀመዉ ወንጀል ዓይነት በየረጃዉ የየራሱን የቅጣት መጠን ይዞ በመመር ምንም እንኳን በሺዎች የሚቆጠሩ ዓመታት ቢያስፈርድም አተገባበሩ ላይ ከሰላሳ እስከ አርባ ዓመታት ስለሚታወቅ። በተጨማሪም የማድሪዱን ጥቃት አቀናብረዋል ተብለዉ ከተጠረጠሩት መካከል ግብፃዊዉ ኤል ሰይድ አንዱ ነዉ ተብሎ በመታመኑ ዳኛዉ በዚህ ጉዳይ ነፃ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አጣርቶ ደርሶበታል ማለታቸዉ ግርምትን ፈጥሯል።

ሶስት ዓመታት ፈጀዉ የፍርድ ሂደትም የትናንቱ ዉሳኔ ያልተጥበቀ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ፍርዱን ከማሳለፍ በተጨማሪም ለጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች ከ30 ሺ እስከ 1.5ሚሊዮን ዩሮ ካሳ እንዲሰጥ በይኗል።