1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማጉፉሊ ጆን ፖምቤ የታንዛንያውን ምርጫ አሸነፉ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 18 2008

«ቡልዶዘር» በሚል ቅጽል ስም በህዝቡ ዘንድ የሚታወቁት የ56 ዓመቱ ማጉፉሊ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። ሳሚያ ሀሰን በታንዛኒያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝደንት ይሆናሉ።

https://p.dw.com/p/1Gwo4
Tansania Wahlen John Pombe Magufuli
ምስል picture-alliance/AP Photo/K. Said

ታንዛኒያ ዉስጥ እሁድ ዕለት በተካሄደዉ ምርጫ ገዢ ፓርቲ ፕሬዝደንታዊ እጩ ምርጫዉን ማሸነፋቸዉን የሀገሪቱ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ ይፋ አደረገ። በመግለጫዉ መሠረትም የቻማ ቻ ማፒንዱዚ በምህፃሩ CCM እጩ ማጉፉሊ ጆን ፖምቤ 58 በመቶ ድምፅ፤ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲ እጩዉ ኤድዋርድ ሎዋሳ ደግሞ 39,97 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸዉ ተገልጿል። ተቃዋሚዉ ፓርቲ ዉጤቱን አጣጥሎ አሸንፌያለሁ እያለ ነዉ። የታንዛኒያ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ዳሚያን ሉቡቫ ዛሬ የምርጫ ዉጤቱን እንዲህ ነዉ ይፋ ያደረጉት።

«የ2015 ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዉጤትን ይፋ አደርጋለሁ፤ 1ኛ ዶክተር ማጉፉሊ ጆን ፖምቤ ዮሴፍ የተባበረችዉ ታንዛኒያ ሪፑብሊክ ፕሬዝደንት ሆነዉ ተመርጠዋል። ሁለተኛ፤ ሳሚያ ሀሰን ሱሉሁ የተባበረችዉ ታንዛኒያ ሪፑብሊክ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነዉ ተመርጠዋል። ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።»

ሎዋሳ በበኩላቸዉ የምርጫ ኮሚሽኑ የድምጽ ቆጠራዉን አሳስቷል ሲሉ ከሰዋል። ተሳስቷል ያሉትን የድምጽ ቆጠራ አሻሽሎ በማጉፉሊ ቦታ ኤድዋርድ ሎዋሳ ማሸነፋቸዉን እንዲያዉጅ ጠይቀዋል። ምንም እንኳን CCM በፕሬዝደንታዊ ምርጫዉ ቢያሸንፍም በርካታ የፓርቲዉ አባላት የሆኑ ባለስልጣናት የምክር ቤት መቀመጫቸዉን አጥተዋል።«ቡልዶዘር» በሚል ቅጽል ስም በህዝቡ ዘንድ የሚታወቁት የ56 ዓመቱ ማጉፉሊ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል። ሳሚያ ሀሰን በታንዛኒያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝደንት ይሆናሉ። በሌላ በኩል የዛንዚባር የምርጫ ዉጤት በመሰረዙ ዴሞክራሲ አደጋ ላይ ነዉ ሲሉ የምርጫ ታዛቢዎች አስጠንቅቀዋል። የአፍሪቃ እና የዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢዎች መሪዎቹ ልዩነታቸዉን ወደጎን በማድረግ ለሰላም እንዲሠሩም ጠይቀዋል።

Tansania Wahlen
ምስል DW/Ch. Ngereza

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ