1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሜክሲካዊቷ ጋዜጠኛ የ«DW» ሽልማትን አገኘች

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2011

«DW» ለሜክሲካዊቷ ጋዜጠኛ እና ደራሲ አናቤል ሄርናንዴዝ የዘንድሮውን የ«DW» «ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት» ሽልማት ሰጠ። በምርመራ ጋዜጠኝነት የተሰማራችው ሄርናንዴዝ ሽልማቱ የተሰጣት በድፍረት ባከናወነቻቸው የምርመራ ስራዎችዋ መሆኑን የ«DW» ዋና ሥራ አስኪያጅ ፔተር ሊምቡርግ ዛሬ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3DgD6
Interview mit der Gewinnerin des DW Freedom of Speech Award 2019: Anabel Hernández
ምስል DW/V. Tellmann

ሄርናንዴዝን «የደፋር ጋዜጠኝነት ተምሳሌት» ሲሉ የጠሩት ሊምቡርግ ሁሌም ጥልቅ ምርመራዎችን በማካሄድ ለጉዳዮች ይበልጥ ቀርባ የምትሠራ መሆኑን መስክረውላታል። አናቤልም ሽልማቱን በየዕለቱ ሥራቸውን በሚያከናውኑ ጎበዝ ጋጠኞች ስም እንደምትቀበል አስታውቃለች። ለዶቼቬለ በሰጠችው አስተያየትም ሽላማቱ ይበልጥ ለመስራት እንደሚያተጋት ገልጻለች።
«ይሽ ሽልማት የመጣው በህይቀቴ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በምለው ወቅት ላይ ነው። ምክንያቱም ከሜክሲኮ ውጭ ብቸኝነት ይሰማኛል። አንዳንድ ጊኤ ምናልባት እንዲቀየሩ ለምፈልጋቸው ነገሮች ሥራዬ በቂ አልነበረም ብዬ አስባለሁ ሆኖም ይህ ሽልማት ለኔ ከሽልማትም በላይ ነው። ይህ ስለኔ ብቻ አይደለም። ይልቁንም ለሜክሲኮ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ከሜክሲኮ ህዝብ መረጃ የማግኘት መብት ጋር የተያያዘ ነው ከዓለም ዓቀፍ ሚዲያ የሚገኝ ይህ ዓይነት ሽልማት ትግሉን እንድንቀጥል ይረዳናል።
በ1990ዎቹ በተለያዩ የሜክሲኮ ጋዜጦች ላይ በአርታኢነት ትሰራ የነበረው ሄርናንዴዝ ዓለም አቀፍ እውቅና ያተረፈችው በጎርጎሮሳዊው 2010 ባሳተመችው እና በሜክሲኮ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎች፣ በፖለቲከኞች እና በፀጥታ አስከባሪ ኃይላት መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ባጋለጠው መጽሐፍዋ ነው። ባለፈው ዓመትም ደብዛቸው ስለጠፋ የታፈኑ 43 ተማሪዎች የጻፈችው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መጽሐፍም አላት። በሥራዎችዋ ምክንያት የግድያ ዛቻ የሚሰነዘርባት ሄርናንዴዝ በአሁኑ ጊዜ በስደት አውሮጳ ውስጥ ነው የምትኖረው። «DW» «ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ» ሽልማት ሲሰጥ የዘንድሮው ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። «DW» ሽልማቱን የሚሰጠው ሰብዓዊ መብት እንዲሁም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ለሚጥሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ነው።  

 

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ