1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ በኖርድራይንቬስትፋለን

ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2004

ከሆላንድና ከቤልጂግ በሚዋሰነው በምዕራባዊው የጀርመን ፌደራል ክፍለ ግዛት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን የፊታችን ግንቦት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጠርቷል ። ለጀርምን ጥምር መንግሥት ህልውና ወሳኝ የተባለው ይህ ምርጫም እዚህ ጀርመን ትኩረት ከተሰጣቸው

https://p.dw.com/p/14OHl
ሀነሎረ ክራፍትና ምክትላቸው ሲልቭያ ሎህርማንምስል picture-alliance/dpa

ከሆላንድና ከቤልጂግ በሚዋሰነው በምዕራባዊው የጀርመን ፌደራል ክፍለ ግዛት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን የፊታችን ግንቦት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጠርቷል ። ለጀርምን ጥምር መንግሥት ህልውና ወሳኝ የተባለው ይህ ምርጫም እዚህ ጀርመን ትኩረት ከተሰጣቸው አብይ ጉዳዮች አንዱ ነው ። ራድዮ ጣቢያችን ያለበት የቦን ከተማ የሚገኝበት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን ከሌሎቹ ክፍለ ግዛቶች ጋር ሲነፃፀር በህዝብ ብዛት የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል ። ይህም የዛሬ 2 ወሩ ምርጫ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ መሆኑን የፍራንክፈርቱ የፖለቲካ ሳይንስና የህግ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ያሰረዳሉ ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ምርጫው የሚካሄድበትን ምክንያትና ውጤቱ በጥምሩ መንግሥት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ይቃኛል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ