1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ 2002እና ዝግጅቱ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7 2001

በቀጣዩ 2002ዓ,ም የሚካሄደዉ ምርጫ ግልፅ፤ ተዓማኒ፤ ፍትሃዊና ሰላማዊ እንደሚሆን ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግ ከወዲሁ እየተናገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/HXk3
ከ1997ቱ ምርጫ ድምፅ ሰጪዎች አንዷ
ከ1997ቱ ምርጫ ድምፅ ሰጪዎች አንዷምስል AP

ምርጫዉን የተሳካ ለማድረግም ስልታዊ ሰነድ ተዘጋጅቶ በገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት መካከል ለዉይይት መበተኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታዉቀዋል። ምንም እንኳን መንግስት ይህን ቢልም ከ1997ዓ,ም ምርጫ የማይረሳ ተሞክሮ ቀስመናል የሚሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኢህአዴግ የሚገልጸዉና በተግባር የሚያደርገዉ አይገናኝም ሲሉ ትችት እየሰነዘሩ ነዉ።