1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምክር ቤቱ ሦስት ሚኒስትሮችን ሾመ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2011

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ መደበኛ ጉባኤው ሦስት አዳዲስ ሹመትን ሰጠ። በዚሁ መሠረትም 1ኛ አቶ ለማ መገርሳን የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስት፤ 2ኛ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ 3ኛ ወይዘሮ አይሻ መሃመድን የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።

https://p.dw.com/p/3H0J8
Äthiopien Vereidigung Premierminister Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/AA/M. W. Hailu

ሹመቱ በአምድ የተቃውሞ እንዲሁም በአምስት የድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የውሳኔ ቁጥር 19 / 2011 ሆኖ የጸደቀው። ብዙ ክርክርና ውይይት ያልተደረገበት ይህ የሹመት አሰጣጥ ከእንድ የምክር ቤት አባል «ሹመት ጎርፍ ኾነ» የሚል ጥያቄ አስነስቷል። በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ የሆኑት ሚኒስትር ጫላ ደሜ ስለ ሹመቱ በሰጡት ምላሽ «አሁን የተሰጠው ሹመት ለውጡን ለማስቀጠል ታልሞ የተደረገ ነው» ማለታቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል።

ሁለቱ ተሿሚዎች በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ግን በቃለ መሃላው ላይ አልተገኙም። ስላለመገኘታቸው የተሰጠ ምክንያትም የለም። የሹመት ሂደቱ በአጠቃላይ 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነበር የተጠናቀቀው።

 ሰለሞን ሙጬ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ