1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሞት እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ፈተና

ሐሙስ፣ የካቲት 28 2011

ሀገር ቤት ሆኖው የውጭውን ዓለም ኑሮ የሚያልሙ ወገኖች ብዙውን ጊዜ በጎ በጎውን ደግ ደጉን ብቻ ይሰሙ ይሆናል። እውነታው ግን በአብዛኛው በየግለሰቡ ቤተሰቦች ዘንድ ተከድኖ የሚቀር ከባድ ሰቀቀን ያካተተ መሆኑ ነው።

https://p.dw.com/p/3EctD
Allerseelen Friedhof im Herbst
ምስል picture alliance/dpa Themendienst

«ማኅበራዊ ተቋማት በውጪም ያስፈልጋሉ»

 ከሀገር ከወገን እና ከሚያውቁት አካባቢ በተለያዩ ምክንያቶች እና አጋጣሚዎች ርቆ በውጪው ዓለም የሚኖረው ወገን ከመልካም ገጠመኙ ጎን ለጎን ዕለት ዕለት የሚሳቀቅባቸው እና የሚያዝንባቸው አልፎ ተርፎም ከሀገር የራቀበትን ቀን የሚያማርር የሚረግምባቸውን ድንገቶች ሊጋፈጥ ይገደዳል። ሀገር ቤት ሳለ በቤተሰብ ኃላፊነት የሚሸፈነው የማኅበረሰብ ግንኙነት በውጭው ዓለም ብቻውን መቋቋም እና መጋፈጥ ይኖርበታል። የዕለቱ የባህል መሰናዶ በውጭው ዓለም ኢትዮጵያውያን እርስ በርስ ለመደጋገፍ እና ለመረዳዳት ሊጠቀሙባቸው ከሚገቡ ማኅበራዊ ተቋማት አንዱ ስለሆነው ስለዕድር ተሞክሮዎችን ተንተርሶ የሚለን ይኖረዋል። ዝግጅቱን ከለንደን ሃና ደምሴ አጠናቅራዋለች።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ