1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሠዎች ለሠዎችና የአጣሪዉ ድርጅት ዉሳኔ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2005

«ሒሳብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃ አለገኘንም። በዕርዳታ የተሰበሰበ ገብዘብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃም አላገኘንም።»

https://p.dw.com/p/19ENg
ወይዘር አልማዝና ባለቤታቸዉምስል picture-alliance/dpa
Karlheinz Böhm mit einer Mutter, Äthiopien
ካርል-ሐይንስ በምምስል Peter Rigaud


ሰዎች ለሰዎች የተሰኘዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት ከቀድሞ ለጋሾቹ ከሚሠነዘርበት ዉንጀለና ወቀሳ ነፃ መሆኑን አንድ የጀርመን አጣሪ ተቋም አስታወቀ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚረዳዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅትን ለረጅም ጊዜ በገንዘብ ከሚደጉሙት አንዱ የድርጅቱ መሪዎች በርዳታ የሚያገኙትን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸዉ አዉለዋል፥ ወይም አባክነዋል የሚዉል ወቀሳ ሲያሰሙ ነበር። በፍቃዳቸዉ የተመዘገቡ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶችን ሥራና አሠራር እየመረመረ የተዓማኒነት እና የጥራት ማረጋገጫ የሚሠጠዉ አጣሪ ተቋማት ትናንት እንዳስታወቀዉ ግን ለጋሹ ድርጅትና መሪዎቹ የተወቀሱበትን ጥፋት አልፈፀሙም።


የሰዎች ለሠዎች ሊቀመንበር ወይዘሮ አልማዝ በም ዛሬ-እንደነገሩን።መደሰት ብቻ ሳይሆን እርካታ፥ ምናልባትም ሕልዉናን መልሶ የማረጋገጥ እፎይታም ጭምር ነዉ።የደስታ፥ እርካታ፥ እፎይታዉ መሠረት የጀርመኑ የድርጅቶች ጥራት ተቆጣጣሪ ተቋም DZI-በጀርመንኛ ምሕፃሩ ትናንት ይፋ ያደረገዉ የምርመራ ዉጤት ነዉ።የአጣሪዉ ተቋም የበላይ ሐላፊ ቡርክሐርድ ቪልከ

«ሒሳብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃ አለገኘንም። በዕርዳታ የተሰበሰበ ገብዘብ ተጭበርብሯል የሚለዉን ወቀሳ የሚያረጋግጥ መረጃም አላገኘንም።»


ቪልከ የሚመሩት DZI-በፈቃደኝነት የተመዘገቡ ድርጅቶችን ሥራና አሠራር እየመረመረ የጥራትና የታማኝነት ዋስትና የሚሰጥ ተቋም ነዉ።ሠዎች ለሠዎችም የዚሕ ተቋም አባል ሆኖ በየአመቱ እየተመረመረ፥ የሚሰጠዉን አስተያየት እየተቀበለ DZI-«ማሕተም የሚለዉን የጥረትና የታማኝነት ማረጋገጪያ ሲያገኝ ሃያ-ዓመት አልፎታል።

የዘንድሮዉ ግን የተለየ ነበር። ምርመራዉ በለጋሾች ወቀሳ ወይም አቤቱታ መሠረት የተደረገ፥ ልዩ፥ ሒደቱም ጠንከር፥ ከረር ያለ ነበር።ሠዎች ለሰዎችን ከሚረዱት ቱጃሮች አንዱና ተባባሪዎቻቸዉ የለጋሹን ድርጅት የሊቀመንበርነት ሥልጣን በቅርቡ የተረከቡትን ወይዘሮ አልማዝ በምን ጨምሮ አመራሩን በርዳታ የተሰጠ ገንዘብን፥ ለግል ጥቅማቸዉ አዉለዋል፥ አጭበርብረዋል፤ ደረጃቸዉን ያልጠበቁ ትምሕርት ቤቶችና የሕክምና ተቋማትን አስገንብተዋል የሚሉ ጠንካራ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸዉ ነበር።

ወይዘሮ አልማዝ የወቃሾቹ ዓላማ ድርጅታችን የጥረትና የተዓማኒነት ማረጋገጪያዉን እንዲቀማ ነበር-ባይ ናቸዉ።

በወይዘሮ አለማዝ አገላለፅ በጥልቀት እና በስፋት የተደረገዉ ፍተሻ የፈታሹ ድርጅት የበላይ ቡርክሐርድ ቪልከ እንደሚሉት የካቲት ተጀመረ።ወቀሽ፥ ተወቀሽ ሠነድ፥ መረጃዎች ያገላብጥ ገባ።

«በቅርቡ፥ ባለፈዉ የካቲት ወቀሳዉ፥ ማለት ከብዙዎቹ በጥቂቱ የገንዘብ ብክነት፥ ወጪን ማዛባት፥ ከወጪ ቀሪ ሒሳብን ማጭበርበር እና የመሳሰሉት ወቀሳዎች ከተሰሙ በሕዋላ ጉዳዩን በጥብቅ መከታተል ጀመርን።በዚሕ ልዩ ምርመራ ከሰወስች ለሰዎች ድርጅት የቀረቡትን ብቻ ሳይሆን ከቀድሞ የድርጅቱ ትልቅ ለጋሽ ያገኘናቸዉን ሠነዶችና መረጃዎችን መርምረናል።»

ስድስት ወር ያሕል መረመሩ።ዉጤት፥-እንደገና ቪልከ፥

«ሠዎች ለሰዎች ድርጅት እስካሁን የተሰጠዉን የጥራትና የተዓማኒነት ማረጋገጪያ እንደያዘ እንዲቀጥል ወስነናል።ለጋሾችም ይሕን ድርጅት በከፍተኛ ደረጃ እምነት ሊጥሉበት ይገባል።»

የምርመራዉ ዉጤት ግብረ-ሠናዩ ድርጅት ድክመት አለበት ያላቸዉን አወቃቀሮችና አሠራሮችንም ጠቁሟል።ዋናዎቹ ቪልከ እንዳሉት ሁለት ናቸዉ።

«ድርጅቱ የቦርድ አወቃቀርና የአሠራር ሒደቱን ማጠናከር አለበት።ፕሮጄክቶችን በማቀዱ በኩልም በተለይ የትምሕር ቤቶች ግንባታ ሲታቀድ የተለያዩ አማራጮችን ለማካተት ክፍት መሆን አለበት።የግንባታ ናሙናዎች (ጨረታ ሲወጣ) ጥራትንም የዋጋ ቅናሽን በተመለከተ እስካሁን ከሚሠራበት የተሻሉ አማራጮች የሚያካትት መሆን አለበት።»

«ተቀብላችኋል።» ጠየቅኋቸዉ ወይዘሮ አልማዝን።-

የድርጅታቸዉ በለጋሾቹ ዘንድ ያለዉን ተቀባይነት ለማጠናከር፥ በተለይ ባለፉት ወራት የጠፋ ስሙን ለማደስ እንደሚጥር፥ ወጪ ገቢዉን ዓለም አቀፍ ዕዉቅና ባለዉ መርማሪ (ኦዲተር) ለማሰራት ማቀዱንም ሊቀመንበሯ ገልፀዋል።

ሰዎች ለሰዎች ወይም ሜንሽን ፉር ሜንሽን ከተመሠረተ ሰለሳ ዓመት አለፈዉ።የቀድሞዉ ኦስትሪያዊዉ የፊልም ተዋኝ ካርል-ሐይንስ በም የመሠረቱት ግብረ ሠናይ ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰወስት መቶ ሃያ-ስድስት ትምሕርት ቤቶች፥ ሰማንያ-ስድስት ጤና ጣቢያዎች፥አስራ-አራት ከፍተኛ ክሊኒኮች ሰወስት ሆስፒታሎችን አስገንብቷል።ከአንድ ሺሕ ሰባት መቶ በላይ የዉሐ ጉሮጓዶች አስቆፍሯል፥ አንድ መቶ ሰላሳ ሚሊዮን ችግኞች አስተክሏል።

25 Jahre Menschen für Menschen
ወይዘር አልማዝና ባለቤታቸዉምስል picture-alliance / dpa/dpaweb
Burkhard Wilke
ቡርክሐርድ ቪልከምስል picture-alliance/dpa

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ