1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሠይፉ ፋንታሁን በዶይቸ ቬለ

እሑድ፣ ግንቦት 25 2011

የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን እንግዳ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 መስራቾች አንዱ የኾነው አርቲስት ሠይፉ ፋንታሁን ነው። ሠይፉ ለዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍመገናኛ ዘዴዎች መድረክ ላይ ለመሳተፍ ቦን ከተማ በመጣበት ወቅት የአማርኛው ክፍል ስቱዲዮ በመገኘት ቃለ-መጠይቅ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3JW0z
Seifu Fantahun
ምስል DW/S. Mantegaftot

ሠይፉ ፋንታሁን በጀርመን ቦን ከተማ

የዶይቸ ቬለ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የውይይት መድረክ ሰኞ ግንቦት 19 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን፣ 2011 ዓ.ም. ተጠናቋል። በእርግጥ የዛሬው ትኩረታችን የውይይት መድረኩ አይደለም። በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ከተጋበዙ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ የኾነው አርቲስት ሠይፉ ፋንታሁን የመዝኛኛ ዝግጅታችን እንግዳችን ነው። ሠይፉ ዶይቸ ቬለ ስለመጣበት ምክንያት እና ስለ ሥራው ያዋየናል።

ቀደም ሲል ያደመጣችሁት ሠይፉ ከዓመታት በፊት ከኮሜዲያን ፍልፍሉ ጋር በኤቢኤስ ዝግጅት ላይ ካቀረበው ቆየት ያለ የኤሌቪዥን ቃለ-መጠይቅ የተቀነጨበውን ነበር። በቀልድ የተዋዙ ቃለ መጠይቆችን በሳምንታዊ ዝግጅቱ በማቅረብ የሚታወቀው አርቲስት ሠይፉ ፋንታሁን ሰሞኑን ወደ ጀርመን፤ ቦን ከተማ የመጣበት አላማ ዶይቸ ቬለ እና ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8ን በሚያገናኝ ጉዳይ ነው።

DW Amharic Seifu Fantahun
ምስል DW/M. Sileshi

ሠይፉ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ከሚያቀርበው የሬድዮ ዝግጅት ባሻገር «ሠይፉ በኢቢኤስ» የተባለ የቴሌቪዥን ዝግጅትም በየሳምንቱ ያስተላልፋል። ይኽን ዝግጅቱን በዩቱዩብ ገጹ ላይ የሚመለከቱ ወደ ሦስት መቶ ሺህ ግድም ተከታታዮች አሉት።  የግል ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ጣቢያዎች ቊጥር እየጨመረ መምጣቱ እንደሚያስደስተው የገለጠው ሠይፉ ሥራው ብርቱ ውጣ ውረድ እንዳለበት ይናገራል።

ከአርቲስት ሠይፉ ፋንታሁን ጋር የtተደረገውን ሙሉውን ቃለ-መጠይቅ ከታች ድምጽ ማገናኛው ውስጥ ማድመጥ ይቻላል

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ሸዋዬ ለገሰ